አዲስ የተመደቡ የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች ከጠቅላላ የማኔጅመንት አባላት ጋር የትውውቅና የውይይት ፕሮግራም አካሄዱ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው የተመደቡት አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ፣ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚና የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም፣
ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ መሃመድ ጀማል እና ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ምርምርና ቢዝነስ ዴቭሎፕመንት ሀላፊ ወ/ሮ መሠረት ደስታ በተገኙበት ነው ፕሮግራሙ የተካሄደው።
በመርሃ ግብሩ ኢንዱስትሪዎች የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን እያቀረቡ ይገኛል።የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ፣የቢሾፍቱ አውቶማቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣የብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ፣የአዳማ ግብርና ማሽነሪዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣የኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣የኢትዮጵያ ፕላስቲክስ ኢንዱስትሪ አፈጻጸም፣ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና የጥራት ስራ አመራር አገልግሎት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ትርፍ ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች የበለጠ ውጤታማ የሚሆኑበትና ትርፍ ያላስመዘቡ ኢንዱስትሪዎች ችግሮቻቸውን በጥልቀት በመፈተሸ የበለጠ መስራት የሚችሉበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በነገው ዕለትም ውይይቱ የሚቀጥል ሲሆን ፣በቀጣይ አዲሶቹን ከፍተኛ አመራሮች ከኢንዱስሪዎች ጋር ማስተዋወቅ የሚያስችል የስራ ጉብኝት ፕሮግራም ይካሄዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *