የካትት 6/2016 ዓ.ም (ኢኢግ)፡
የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ከከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ ጋር በመተባበር በአዲሱ አደረጃጀት ተመድበዉ ወደ ስራ ለገቡ የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙዎች ሰርትፊኬት ተሰቷቸዋል፡፡
የስልጠናዉ ፕሮግራም ለሶስት ቀናት የተከናወነ ሲሆን በመረጃ ቋት (Data center facility)፣ በመረጃ መረብ እና ደህንነት (Network and security) እና በመሰረታዊ የኮምፒዩተር ሥርዓት (Computing system) ላይ ከዋና መ/ቤትና በግሩፑ ስር ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የተዉጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ እና የሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ ታምራት ዲላ በመገኘት ሰርትፊኬቱን ያበረከቱ ሲሆን፤ባስተላለፉት መልእክትም የሰዉ ሃይል ማብቃት ላይ ዘርፉ የጀመራቸዉ ጥሩ ስራዎች ጠንክሮ መቀጠል እንዳለበት በመግለጽ ግሩፑ ለመተግበር ያቀዳቸዉን የቴክኖሎጂ ዕድገት እንዲረጋገጥም ባለሙያዎቹ ድርሻቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል፡፡
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ኃላፊ አቶ አብደላ ሳኒ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሰዉ ሃይል የማብቃት ስራ ቀጣይነት እንዲኖረዉ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ያብራሩ ሲሆን ከባለድርሻ አካላትና ሃገር በቀል ተቋማት ጋር ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው ቀደም ሲል የነበራቸዉ የስራ ተነሳሽነት ላይ ስልጠናዉ ተደምሮ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያችል ጥሩ አቅም የሚፈጥርላቸዉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡