በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የአውቶቡሶች፣ የቀላል እና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ ለቱሪዝም የሚውሉ ተሽከርካሪዎች፣ የግንባታ ማምረቻ መሣሪያዎችን በማምረት ኢንዱስትሪውን እየደገፈ ይገኛል።
ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ በተመሣሣይ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የታንክና ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ማምረቻ ዎርክሾፕንም ጎብኝተዋል።
በዋለልኝ ታምር
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን






