የኮርፖሬት ምርምር እና ልማት ማዕከል

ማዕከሉ የተቋቋመባቸው አላማዎች

የኮርፖሬት ምርምር እና ልማት ማዕከል የተቋቋመባቸው ዋና ዋና አላማዎች ከግሩፑ የመቋቋሚያ አላማዎች የተቀዳ እና በአመዛኙ የአላማዎቹ ተግባራት በማዕከሉ ሚና ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው። እነሱም;-

 • የማምረቻ ወይም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ዲዛይን ማድረግ፣ የምርቱን አካላት ቴክኒካዊ መዘርዝሮችን ማርቀቅ፣ የአመራረት ቴክኖሎጂዎችን መንደፍ፣ ተያያዥ የቴክኖሎጂ እና የምርት ሰነዶችን ማዘጋጀት፤ 
 • ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ፈጣን ልማት የሚያግዙ ተጨባጭና የወደፊት ፍላጐቶችን በማጥናት ማልማት ምርትና አገልግሎትን የሚያሳልጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመምረጥ የንድፍ/ዲዛይን ስራ መስራት፤
 • የቴክኖሎጂ አቅም ማስፋፋትና ማጎልበት በሚያስችል መልኩ ከትምህርት ተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር እና ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ተቋማት ጋር በአጋርነት መሥራት፤
 • በድርጅቱ ምርት እና አገልግሎቶች ላይ ልዩነት የሚፈጥሩ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መለየት/መምረጥ፣ ዝርዝር ጥናት ማከናወን፣ ቴክኖሎጂን ማልማትና ማስተላለፍ፤
 • የድርጅቱን የእድገት አመላካች ነጥቦች መለየት ማንጠር እና የትግበራ ዕቅዶችን ቴክኒካዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ይዘት መቅረፅ ናቸው።

የማዕከሉ ተልዕኮ

 • የአምራች ኢንዳስትሪውን፣ እና የአገልግሎት ዘርፉን እድገት የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግና ማስተላለፍ
 • ከፍተኛ የገበያ ክፍተት ያስከተሉ፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ፣ እና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ልማት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ የሚመረቱባቸውን የቴክኖሎጂ እና የአመራረት አግባቦችን ማጥናት፣ ማበልፀግ እና ማልማት፤
 • የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ፕላንቶችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማሻሻል፣ የምርት ቴክኖሎጂ መንደፍ እና ማሻሻል፤
 • የድርጅቱን ምርት እና አገልግሎት ስራዎች ከመጪ ቴክኖሎጂ አንፃር መቃኘ እና የተሻሻሉ የምርት እና አገልሎት ዘርፎችን ማመላከት።
 • ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጣኛዎች፣ በምርመር እና ስርጸት ተግባር ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች፣ የዘርፉ ቴክኖሎጂ አልሚዎች እና ከሳይንስ እና ኢኖቬሽን ሚንስቴር ጋር ለዘርፉ ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ፤

ራዕይ

 • በ2022 በተግባራዊ ምርምርና ልማት ዘርፍ (Applied Research)፣ በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ በመገኘት ሃገራዊ የኢንዱስትሪ ልማት ስኬትን የሚደግፍ የምርምርና ልማት ማዕከል መገንባት:

ዕሴቶች

 • ደንበኛ ተኮርነት /Customer Focused
 • ጥራት /Quality
 • የቡድን ስራ /Team Work
 • ኢኖቬሽን /Inovation
 • ውጤታማነት /Efficiency
 • ቅልጥፍና /Efectivnes
 • ታማኝነት /Integrity

የማዕከሉ ዋና ዋና  ተግባራት

 • በማዕከልና በየፋብሪካው የሚከናወኑ የምርምርና ልማት፣ የዲዛይንና ልማት፣ የፕሮዳክት ማሻሻል ስራዎችና የማምረቻ ቴክኖሎጂ ስራዎችን የአተገባበር ስልት ያቅዳል፤ ያደራጃል፣ ያሰማራል፣ ይከታተላል፣ ያስፈፅማል፤
 • የምርምርና ልማት ውጤቶችን በአውደ ርዕይ እንዲቀርቡና ግኝቶችን እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
 • የመሳሪያዎችና የምርቶች ዲዛይን ያከናወናል እንዴት እንደሚመረቱም ቴክኖሎጂ ይነድፋል (የአመራረት ሂደቱን፣ አሰላለፉን (layout)፣ ተፈላጊ ዕቃዎችን (tooling)፣ የጥራት ሰነዶችን፣ የማምረቻ መሳሪያዎቹን፣ የሰው ሃይል ስብጥሩን በማጣመር መንደፍ) በተፈጻሚነት ሂደቱም የቴክኖሎጂ ሱፐርቪዥን ስራዎችን ያከናውናል፤
 • በፕሮዳክሽን ማኔጅመንት፣ በኦፕሬሽን ማኔጅመንትና በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ አነዳደፍ ዙሪያ ምርጥ ተመክሮዎች ተጠንተው ዲዛይን እንዲደረጉና በስልጠና የብኢኮ አቅም ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል፤
 • ከውጭ የሚገኙ የቴክኖሎጂ እውቀቶችንና ልምዶችን ያሰባስባል፣ ያላምዳል፣ያሰራጫል፤
 • አገር በቀል የማኑፋክቸሪንግ እውቀትና ቴክኖሎጂዎችን ያጠናል፣ ያበለፅጋል ወደ ኢንዱስትሪ እስኬል እንዲያድግ ያደርጋል፤
 • የሃገሪቱን የቴክኖሎጂ ልማት የሚያፋጥኑ የምርምር ስራዎችን ያካሂዳል፣ የቴክኖሎጂ አቅምንበመገንባትናበማከማቸትለተጠቃሚ ያሰራጫል፤
 • በምርምር የሚገኙ እውቀቶችን በማደራጀት፣ የአጠቃቀም ስልቶችን ማዘጋጀት ለተጠቃሚው በስልጠናና በሱፐርቪዥን ያስተላልፋል፤
 • በፋብሪካ ደረጃ ያሉ የዲዛይን እና ልማት ስራዎችን በበላይነት ያስተባብራል፣ በፋብሪካ ደረጃ ሊለሙ የሚገባቸውን የተለያዩ የምርት ቴክኖሎጂዎችን በጋራ ያለማል፣

ማዕከሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

 • የምርምር አሰራርና አመራር የምክር አገልግሎት መስጠት
 • የዲዛይንና የኢንጂነሪንግ አመራርና አሰራር ማማከርና ስልጠና መስጠት
 • በዲዛይንና በኢንጂነሪንግ ስራ ላይ የተሰማሩ ወይም ሊሰማሩ ላሰቡ አካላት በዲዛይን ኢንጂነሪንግ አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ
 • ምርምር፣ ዲዛይንና ኢንጂነሪንግ፣ መመሪያዎችን በመቅረፅ በመስኩ ለተሰማሩ አካላት የማማከር አገልግሎት መስጠት
 • የኢንጂነሪንግ ተቋማት በሚያከናውኑት ስራዎች ላይ የተመሰረተ የአሰራር፣ የአፈፃፀምና የአመራር ድጋፍ መስጠት
 • በኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስራዎች ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ተቋማት የእውቀትና የስልጠና ድጋፍ መስጠት
 • የኮንሴፕት ዲዛይንን በማዘጋጀት ለልማት አቅሞች ማቅረብ
 • የቴክኖሎጂ ክፍተትን በማጥናት የመፍትሄ ሀሳብ ማፍለቅ፤ ተግባራዊ የሚሆንበትን ስልት መንደፍ
 • የአዋጪነት ጥናት ማድረግ፤ ተግባራዊ የሚሆንበትን ስልት መንደፍ
 • የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ሱፐርቪሽን ስራዎችን መስራት