ሃይ ቴክ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

በ2003 ዓ.ም  የብኢኮ እንዱ ኢንዱስትሪ ሆኖ የተቋቋመ ሲሆን የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ምርቶችን በማምረት ተግባር ላይ የተሰማራ ተቋም ነዉ፡፡ ለኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በግብዓትነት የሚያገለግሉ የሬዲዮ ሰርኪዩት ቦርዶችን፣ በጦር መሳሪያ ላይ የሚገጠሙ መነፅሮችን፣ የመገናኛ ሬዲዮኖችን ፣ የተለያየ መጠን ያላቸዉ ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖችን፣ የትራፊክ መብራቶች፣ ኢነርጂ ሜትሮችን፣ ተርማል ኢሜጀሪዎችን፣ ሴቶቦክሶችንና ሴኪዩሪቲ ካሜራዎችን ያመርታል፡፡ በተጨማሪም ለአቭየሽን ቴክኖሎጂ በግብዓትነት የሚያገለግሉ ኦፕሪንግ ሲሊንግ ጋስኬትና ለቀላል ፣ ለመካከለኛና ለከባድ መሳሪዎች አካል የሚዉሉ የፕላስቲክ ዉጤቶችን ፤ ለህክምና መገልገያ የሚዉሉ መሳሪያዎችን እያመረተ የሚገኝ ሲሆን በቴክኖሎጂ ሽግግሩና በኢንዱስትሪ ልማቱ  አገራዊ አቅምን በማጎልበት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡ 

ተልዕኮ

 • የኤሌክትሮኒክስ፣ የኤሌክትሮ ኦፕቲክስ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ማምረቻ ቴክኖሎጂ በመገንባት እና ቴክኖሎጂውን በማልማት ወታደራዊና ሲቪል ምርቶችን በጥራትና በአነስተኛ ዋጋ አምርቶ በማቅረብ የኢንዱስትሪው ልማት ላይ የራስ ድርሻ መወጣት
 • በመስኩ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ፣ የገበያ ክፍተት ያላቸው ፓርቶችና ኢኩፕመንቶችን በተወዳዳሪነትና በጥራት ማምረት
 • በኢሌክትሮኒክስ፣ የኦፕቶ ኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ ወታደራዊና ሲቪል ምርቶችን በጥራት በማምረት አገራችን የምታስወጣው የውጭ ምንዛሪ ማስቀረትና ገቢ ማስገኘት
 • በመስኩ የስልጠና፣ የማማከርና የኮሚሽኒግ ስራ በመስራት ኢንዱስትሪውን ማልማትና ገቢ ማስገኘት፡፡

የምርት ፋብሪካዎች

 • ኤሌክትሮኒክስ ፋብሪካ
 • ኢነርጂ ሜትር ፋብሪካ
 • የኦፕቶ- ኤሌክትሮኒክስ ፋብሪካ
 • ኮሙኒኬሽን እቃዎች ፋብሪካ
 • ለቤት ውስጥ, ለሕክምና አገልግሎት እና ለቢሮ  አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ማምረቻ ፋብሪካ

ምርቶች

 • ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች (LED)
 • የአይቲ ፕላስ ስማርት ኢነርጂ ሜትር
 • ዳታ ኮንሰንትሬተር
 • የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች
 • ዲቪዲ-T2 ሴትቶፕ ቦክስ
 • ራደር
 • ኮሚዩኒኬሽን መሣሪያዎች
 • የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች ማምረት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *