ህብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

እ.ኤ.አ ከ1945 ዓ.ም ጀምሮ የተጠነሰሰው ይህ ተቋም አዲስ ማሽን ኢንጂነሪንግ እና ህብረት ማሽን ቱልስ ኢንጂነሪንግ ከምፕሌክስ በሚሉ ልዩ ልዩ ስያሜዎች በቀድሞ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተደራጅቶ ሲሰራ ቆየ፡፡ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርሬሽን በሚኒስትሮች ደንብ ቁጥር 183/2002 ዓም ሲቋቋም ህብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ በሚል ስያሜ ተጠናክሮ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ ተቋሙ በተሰጠው አዲስ አቅጣጫ መሰረት አደረጃጀቱንና ኮር ተግባራቱን አስተካክሎ መስራት ጀመረ፡፡

የሀገሪቱን የኢንዱስትሪያል ማሽነሪዎች አቅርቦትና የካፒታል ቁሳቁሶች ፍላጎት ለማሟላት ኢንዱስትሪው በስሩ አስር የማምረቻ ፋብካዎችን አቅፎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ዋና መስሪያ ቤቱን አዲስ አበባ ያደረገው ህብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚያስተዳድራቸው ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን ፋብሪካዎቹ በተሰማሩባቸው ዘርፎች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ኢንዱስትሪው እሱን መሰል የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች እንዲያስፋፋ በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት ከ82 በላይ የፍሌክሲብል ማኑፋክቸሪንግ ወርክሾፖች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ገንብቶ አስረክቧል፡፡

ተልዕኮ

 • መለዋወጫዎችንና አባሪ ዕቃዎችን በላቀ ጥራት፣ በተወዳዳሪ ዋጋና በሚፈለገው ብዛት ጊዜና ቦታ አምርቶ በማቅረብ በመስኩ ያለውን የቴክኖሎጂ ችግር መፍታት
 • ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ዕድገትን በሚያፋጥን አግባብ የቴክኖሎጂ ልማትና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን የላቀ ተሳትፎ ማድረግ
 • ሀገራችን ለመላዋወጫዎችና ለማሽነሪ ግዢ የምታወጣውን የውጪ ምንዛሬ ማስቀረት፤ ብሎም የውጪ የገቢ ምንጭን ማሳደግ

የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች

 • የማሽን ግንባታ ፋብሪካ
 • የማቴሪያል ትሪትመንትና ኢንጂኔሪንግ ፋብሪካ
 • ፕሪሲሽን ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካ
 • የማሽን ቦዲና ስትራክቸር ፋብሪካ
 • ኮንቬንሽናል ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካ
 • የቦልትና ነት ማምረቻ ፋብሪካ
 • አዋሽ የፍሬን ሸራ ማምረቻ ፋብሪካ
 • ደብረብርሃን ቤሪንግ ማምረቻ ፋብሪካ
 • ደብረብርሃን አክችዌተር ማምረቻ ፋብሪካ
 • ማሽን አውቶሞሽን ፋብሪካ

ምርቶች

 • ኢንዱስትያል ማሽነሪዎች
 • ሲኤንሲ ሌዝ ማሽን
 • ሲኤንሲ ሚሊንግ ማሽን
 • የጨውና አዮዲን ማደባለቂያ ማሽን
 • ድሪሊንግ ማሽን
 • የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ማሽኖች
 • የአግሮ ፕሮሰሲን ማሽኖች
 • የቆዳ ፋብሪካ ማሽኖች

 መለዋወጫዎች

 • ለስኳር ፋብሪካዎች
 • ለጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች
 • የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማሽን
 •  የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማሽኖች
 • የሲሚንቶ ፋብሪካ ማሽኖች
 • የኮንስትራክሽን ማስነሪዎች

የሌሎች ተሸከርካሪዎች መለዋወጫዎች

 • ቦልትና ነት
 • የቤሪንግ ምርቶች
 • ቦል ቤሪንግ
 • ሮለር ቤሪንግ
 • ታፐር ኤንድ ሮለር ቤሪንግ

የፍሬን ሸራ ምርቶች

 • ብሬክ ፓድ
 • ብሬክ ሹ
 • ድራም ታይፕ ብሬክ ሹ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *