ቢሾፍቱ አዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

ፕሮጀክት 40720 የሚል ስያሜ የነበረዉ ሲሆን በ2002 ዓ.ም ቢሾፍቱ አዉቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በመባል ወደ ብኢኮ የተቀላቀለ ኢንዱስትሪ ነዉ፡፡ ኢንዱስትሪዉ ራሱን ወቅቱና ጊዜዉ ካወጣቸዉ የቴክኖሎጂ አስተሳሰቦችና ዉጤቶች ጋር በማዋሃድ አቅሙን እያሳደገና እያጎለበተ ያለ ተቋም ነዉ፡፡በሃገራችን ገና በጅምር ላይ በነበረዉ የአዉቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ተሰማርቶ የሚደነቅ ተግባር ለማከናወን የበቃ ሲሆን የህዝቡን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ 12 ሜትርና 18 ሜትር ርዝመት ያላቸዉን የከተማ አዉቶብሶችና አገር አቋራጭ አዉቶብሶችን ያመርታል፡፡በተጨማሪም ለብዝሃ ኢኮኖሚዉ እንቅስቃሴ አጋዥ የሆኑ ሚኒና ሚድ ባሶች፣ ፒክአፖች፣ ስቴሽን ዋገኖች፣ አምቡላንሶች፣ ሃይቤድና ሎዉቤዶች፣ ዳምፕትራኮች፣ ሚኒትራኮች፣ ካርጎ ትራኮችና የመሳሰሉትን ኮሜርሻል ምርቶችን በማምረት የገበያ ክፍተትን ከመሙላት፣የዉጭ ምንዛሬን ከመቀነስ፣ ከእዉቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ከስራ ዕድል ፈጠራና አገራዊ አቅምን ከማጎልበት አኳያ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ለመከላከያና ፀጥታ ሃይሎቻችን የሚዉሉ የተለያዩ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን፣ ታንኮችን፣ኦራሎችን፣አምቡላንሶችንና የመሳሰሉ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ያመርታል፡፡

ከዚህ ባሻገር ኢንዱስትሪው በዋናነት በአውቶቲቭ ቴክኖሎጂ ልማት ላይ ይሰራል፡፡ በሀገራችን የትራንስፖርት ኢንዱስትሪ ቀዳሚ የሆነው የየብስስ ትራንስፖርት በተሸከርካሪዎች የሚፈፀም በመሆኑ መስኩን በቀጣይነት የሚያለማ ተቋም ያስፈልጋል፡፡  በዚህም ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከላይ የተጠቀሱ ምርቶች የሚመረቱባቸውና የሚገጣጠሙባቸው ፋሲሊቲዎች ወይም ፕላንቶች የማስፋፋት አቅም አዳብሯል፡፡

ኢንዱስትሪዉ  የህዝቡን የኢንዱስትሪ ባለቤትነት የሚያረጋግጡ፤ በበአዉቶሞቲቭ ዘርፉ የመሪነት ድርሻዉን በመዉሰድ ለበርካታ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የስራና የገበያ ዕድል በመፍጠርም ጭምር በሃገራችን በርካታ የአዉቶሞቲቭ ማምረቻዎችን ለመገንባትና ለማስተላለፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

 • የተሽከርካሪዎች ማምረቻ ቴክኖሎጂን በማልማት የአዉቶሞቲቭ ኢንዱስትሪን ማስፋፋት
 • ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ያላቸዉና የገበያ ክፍተትን መሙላት የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን ማምረት
 • ለኮሜርሻልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚዉሉ ግብዓቶችንና ሰብ ሲስተሞችን ማምረት
 • ሀገራዊ የአዉቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ዕድገትን በሚያፋጥን አግባብ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን ሀገራችንን ከተሸከርካሪዎች ግዥ ጥገኝነት ማላቀቅ
 •  በአካባቢያዊ የአዉቶሞቲቭ ገበያ ዉድድር በመግባት ከዘርፉ ሊፈጠር የሚችልን ገቢ ከፍ ማድረግ

የማምረቻ  ፋብሪካዎች

 • የቀላል ተሽከርካሪዎች ማምረቻ ፋብሪካ
 • የከባድ ተሽከርካሪዎች  ማምረቻ ፋብሪካ
 • ፓወር ትሬን ማምረቻ ፋብሪካ
 • የተሽከርካሪ ሲስተም ማምረቻ ፋብሪካ
 • ቦዲና ፍሬም ማምረቻ ፋብሪካ
 • የታንክና ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ማምረቻ ፋብሪካ
 • ቀለም መቀቢያ ፋብሪካ
 • የአዉቶብስ ማምረቻ ፋብሪካ

ምርቶች

 • 12ሜትር እና 18ሜትር ርዝመት ያላቸዉ የከተማ አዉቶብሶች
 •  ሚድ ባሶች
 • ሃገር አቋራጭ አዉቶብሶች
 • ባለ1ና ባለ2 ጋቢና ፒካፖች
 • ስቴሽን ዋገኖች
 • ዳምፕ ትራኮች
 •  የነዳጅና የዉሃ ቦቴዎች
 • ካርጎ ትራኮች
 • ሃይቤድና ሎዉቤዶች
 • ሚክሰር ድራም
 • ታንክና የተለያዩ ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች
 • ሚኒ ትራኮች (ባለ 2,3,5 ቶን )
 • ለሁሉም አይነት ትራኮች የሚሆኑ ጋቢናዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *