አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ ስር ሲተዳደር የነበረውና ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ወደ ብኢኮ ከገቡ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መካከል አንዱ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ነዉ፡፡ኢንዱስትሪዉ  በመሰረታዊ ብረታ ብረት ቴክኖሎጂ ልማት ሃገራችንን ወደ ላቀ የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገርና  በገበያም ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ የመገኘት ራዕይ አንግቦ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንዱስትሪዉ ዘመናዊና የተሟሉ የመለኪያና የመፈተሻ መሳሪያዎች ባለቤት ሲሆን በሂት ትሪትመንት ፣ በኤሌክትሮ ፕሌቲንግ፣ በቅጥቀጣና በፕረሲንግ፣ የካስቲንግ ፣ የስቲል ፕሮሰሲንግ ፣ የማሽነሪንግና የሜታለርጂካልስራዎችን ያከናዉናል፤ በዘርፉም ስልጠናና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ኢንዱስትሪው ሀገር በቀል የብረታ ብረት ስራ ከዘመናዊ የብረታ ብረት ቴክኖሎጂ ጋር በማስማማት በዘርፉ ቴክኖሎጂ የማልማትና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን የማስፋፋት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ልዩ ልዩ የብረታ ብረትና ብረት ነክ ማቅለጫዎች በሀገሪቱ ለማስፋፋት እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ሽግግሩ ከፍተኛ የብረት ውጤቶች በሚፈልግበት ጊዜ ላይ የምንገኝ በመሆናችን ወደ ብረት ማዕድን የማውጣት ተግባር መሸጋገር እንዳለብን ግንዛቤ ተወስዶ በስፋት እየተሰራበት ነው፡፡ኢንዱስትሪው እርስበርሳቸውም ሆነ ለሌሎች የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርቡ የመሰረታዊ ኢንዱስትሪዎች ልማት የማስፋፋት ተልዕኮዉን ጎን ለጎን ይፈፅማል፡፡

ኢንዱስትሪው በስሩ 5 ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግብዓት የሚሆኑ ፓርቶችና መለዋወጫዎች፣ ለትራንስፖርት ሴክተር ግብዓት የሚሆኑ ፓርቶችና መለዋወጫዎች፣ ለግብርናዉ ዘርፍ የሚዉሉ የማሽን መለዋወጫዎች፣ ለስኳር ፋብሪካዎች ግብዓት የሚሆኑ መለዋወጫዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አካላትና መለዋወጫዎች፣ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚዉሉና ለሌሎች የግድብ ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ ግዙፍ የሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ስራዎችና ለተመሳሳይ መለዋወጫዎችና የካፒታል ዕቃዎችና ፕላንቶች በማምረትና በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

 • የሀገራችንን የአሁኑንና የወደፊት የመሰረታዊ የብረታ ብረት ውጤቶች ፍላጎት በማጥናትና በመተንተን የካስቲንግ የሜታለርጅካል ቴክኖሎጂን የማሻሻል ስራን ያለማቋረጥ በማከናወን የሀገር በቀል የፈጠራ ባለቤት መሆን።
 • መሰረታዊ የብረታ ብረት ቴክኖሎጂ ማልማት እንዲሁም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚደግፉ የኢንጂነሪንግ እውቀቶች ትስስር በመፍጠር የሀገራችንን እድገት ከግብ ማድረስ።
 • ከተጨባጭ የስራ እንቅስቃሴ የሚገኙ የስራ ልምዶችን በመጠቀም የሀገራችንን መሰረታዊ የብረታ ብረት ልማት ማፋጠን።
 • ለሰው ሀይል ልማት ቅድሚያ በመስጠት የሰለጠኑና ክህሎት ያላቸውን ባለሙያዎች ማብቃት።

ኮር ቢዝነስ

 • በስቲል ፕሮሰሲንግ የተለያዩ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ምርት ዉጤቶችን ማምረት ፣
 • የካስቲንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ የካስት አይረን ዉጤቶችን ማምረት ፣
 • ዘመናዊ የካስቲንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የነን-ፌረስ ካስቲንግ የኢንጂነሪንግ ዉጤቶችን ማምረት፣
 • በማሽን ፓርትስ ካስት ፕሮዳክሽን የተለያዩ የመለዋወጫ ዕቃዎችን ማምረት፡፡

የማምረቻ  ፋብሪካዎች

 • የብረት ማቅለጫ ፋብሪካ
 • ነን ፌረስ ካስቲንግ ፋብሪካ
 • የማሽነሪ አካላት ማምረቻ ፋብሪካ
 • ስቲል ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ
 • ዝቋላ ስቲል ማምረቻ ፋብሪካ

ምርቶች    

 • ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግብዓት  የሚሆኑ ፓርቶችና መለዋወጫዎች     
 • ለትራንስፖርት ሴክተር ግብዓት የሚሆኑ ፓርቶችና መለዋወጫዎች     
 •  ለግብርናዉ ዘርፍ የሚዉሉ የማሽን መለዋወጫዎች     
 • ለስኳር ፋብሪካዎች ግብዓት የሚሆኑ  መለዋወጫዎች     
 •  የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አካላትና መለዋወጫዎች     
 • ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚዉሉና ለሌሎች የግድብ ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ ዳምጌቶችና ፓይፖች     
 • ሌሎች ተመሳሳይ መለዋወጫዎችና የካፒታል ዕቃዎችና ፕላንቶች ማምረት ፣መገንባት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *