አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

ናዝሬት ትራክተር ፋብሪካ (ናትፋ) በመባል ይጠራ የነበረ ሲሆን በ2002ዓ.ም አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ኢንዱስትሪ በሚል ስያሜ ወደ ብኢኮ የተቀላቀለ ኢንዱስትሪ ነዉ፡፡ የሃገራችን የግብርናዉ ዘርፍ ለማክሮ ኢኮኖሚዉ ዘርፍ ዕድገት የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ድርሻ እንዲያበረክት፣ ዘርፉን በተሻሻሉ ዘመናዊ ግብዓቶች እንዲታገዝ በማስቻል አርሶ አደሩ በወቅቱ እንዲያርስ፣ እንዲዘራና እንዲያጭድ በማድረግ ምርትና ምርታማነቱን ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ዝናብን ብቻ በመጠበቅ ከሚከናወን እርሻ በመላቀቅ የመስኖ እርሻን ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑንና በመንግስት ለተቀመጠዉ አቅጣጫ አጋዥ ሚና እንዳለዉ በመገንዘብ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከዚህ በመነሳትም አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያየ ሞዴልና የፈረስ ጉልበት ያላቸዉን ትራክተሮች፣ ለመስኖ እርሻ የሚያገለግሉ የዉሃ ፓምፖችን፣ መከስከሻና ማረሻዎችን እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ለግብርና ክፍለ ኢኮኖሚዉ መዘመን ጉልህ ድርሻ ያላቸዉ ምርቶችን እያመረተ ይገኛል፡፡  የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች በቀጥታ አምርቶ ከማቅረብ ባሻገር እነዚህ መሳሪያዎች የሚመረቱባቸው የማምረቻ ፋሲሊቲዎች እየገነባ ለግል ባለሀብቶች ያስተላልፋል፡፡

በተጨማሪም በሁለተኛዉ የእድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ አካል የሆነዉ ግብርናዉን በኢንዱስትሪ ለማልማት የሚጠቅም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካዎችን በየክልሉ ለመገንባት ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በብዛት ምርት ያለባቸዉን አካባቢዎች በመለየትና የአዋጭነት ጥናት በማካሄድ ህዝቡን በተለይም ወጣቱን የንብረት ባለቤት ከማድረግና የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ በዘርፉ ኢንዱስትሪ ልማት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

አግሮ ፕሮሰሲንግ  የእርሻ ሜካናይዛሽንና፣ የምግብና መጠጥ ማወቀናበሪያ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ የግብርና ዉጤቶች ማቀነባበሪያና የደን ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎችን ኣጣምሮ የያዘ ወይንም ኣንድ ላይ ተደምረው የሚጠሩበት የኢንዱስትሪ ክፍል ነው፡፡የእርሻ ሜካናይዛሽን ካፒታል ዕቃዎችና ዋና ዋና የምርት መገልገያ ማሽኖቹም እንዲሁ በኢንጅነሪንግ ኢንዲስትሪ ኣማካኝነት የሚመረቱ ናቸው፡፡ የምግብና መጠጥ ኢንዲስትሪ እንደስሙ ሁሉ መጠጥና ምግቦችን በኢንዲስትሪያል መጠን የሚያመርት የኢንዲስትሪ ክፍል ነው፡፡ አዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኢንዱስትሪም ለዘርፉ ቅድሚያ ሰጥቶና እንደ ዋና ስራ ወስዶ  እየሰራበት ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

 • የግብርና  ምርት ዉጤቶችን እሴት መጨመር የሚችሉ የአግሮ ፕሮሰሲንግና የምግብ ማቀነባሪያ ማሽነሪዎችን በማምረት ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ
 • ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችን፣ የምግብ ማቀነባበሪያ መሳሪያዎችን፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማምረቻ ፕላንቶችን ዲዛይን በማድረግ፣ በማምረት፣ በመገጣጠም፣ በመትከል፣ በመፈተሽ በማደስና ዘመናዊ በማድረግ እንዲሁም በማስተማር ቴክኖሎጂዉን ማስፋፋት የአርሶ አደሩን ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችል የእርሻ መሳሪያዎችን ዲዛይን የማድረግ፣ የማምረት፣ የመገጣጠም፣ የማደስና ዘመናዊ የማድረግ ሥራዎችን ማከናወን
 • ሀገራዊ የኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እድገት በሚያፋጥን አገባብ የእርሻ ቴክኖሎጂን ማሳደግና ሀገራችን ከእርሻና ከመስኖ መሣሪያዎች ግዥ ጥገኝነት ማላቀቅ በሚያስችል አቅጣጫ ማከናወን
 • የእርሻ መሳሪያዎች ቴክኖሎጂን በማሳደግ ምርትና አገልግሎትን በጥራት በማቅረብ በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያስችል መንገድ መንቀሳቀስ
 • ጥራት ያለዉ ምርትና አገልግሎት በማከናወን ሰፊ ገበያ መፍጠር መቻልና ከሚገኘዉ ገቢ ለዉስጥ አቅም ግንባታ በማዋል አቅምን በየጊዜዉ ማሳደግ
 • የእርሻ መሳሪያዎች አጠቃቀምና የምርታማነታቸዉን ስልትና ጥናት ለተጠቃሚዎች ስልጠና መስጠት
 • የግብርና ምርት ዉጤቶችን እሴት መጨመር የሚችሉ ማሽነሪዎችን በማምረት ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ

የማምረቻ ፋብሪካዎች

 • ትራክተር ማምረቻ ፋብሪካ
 • የትራክተር ተቀፅላዎች ማምረቻ ፋብሪካ
 • የተለያዩ አይነት ፓምፖች ማምረቻ ፋብሪካ
 • የተለያዩ የመስኖ ዉሃ ማጠጫዎች ማምረቻ ፋብሪካ

 ምርቶች

 • የተለያየ የፈረስ ጉልበት ያላቸዉ ትራክተሮች
 • እንደ ማረሻና መከስከሻ የመሳሰሉ የትራክተር ተቀፅላዎች
 • የተለያየ መጠን ያላቸዉ ስፕሪን ከለር(የዉሃ ማጠጫዎች)
 • የተለያዩ አይነት ሴንትሪፉጋል ፓምፖች

One Reply to “አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *