ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ ስር ሲተዳደር የነበረው የያኔው ኢትዮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ወደ ብኢኮ ከገቡ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መካከል አንዱ ሲሆን የኢትዮዽያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በሚል ስያሜ አዲስ ተልዕኮና ኮር ተግባራት ተሰጠተውት ሊደራጅ ችሏል። ተቋሙ ወደ ብኢኮ ሲቀላቀል በፕላስቲክ ኢንጂነሪንግ ውጤቶች የኢንዱስትሪ ልማቱን እንዲያግዝና የራሱን ሚና እንዲጫወት፣ በአገሪቱ እየተሰሩ ላሉ ታላላቅ የልማት ስራዎችና ሜጋ ፕሮጀክቶች በምርቱ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በማሰብና በፕላስቲክ ውጤቶች ልማት የላቀ የቴክኖሎጂ ሚና እንዲጫወት ለማድረግ ነው፡፡   

ኢንዱስትሪው ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚያስመዘግባቸው ለውጦች በፕላስቲክ፣ በፋይበር፣ በኮምፖዛይት፣ በራበርና መሰል ተያያዝ ውጤቶች ምርት ሳይወሰን ያለውን ሀገራዊ ፍላጎት በተገቢ መንገድ ማሟላት የሚችሉ የማምረቻ ፋብሪካዎችን ገንብቷል፡፡ በዚህ መስክ ለተሰማሩ የግል ባላሀብቶች፣ አክሲዮን ማህበራት፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፕላስቲክ ማምረቻ ፋብሪካዎችን ተክሎ ማስረከብ ወደሚችልበት ደረጃም ተሸጋግሯል፡፡ ኢንዱስትሪው በተለይም የፍጆታ የሚመስሉ ነገር ግን ከአግሮ ፕሮሰሰሪንግ፣ ከመሰረታዊ ኢንዱስትሪ አንዳንዴም ከኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ጋር የሚገናኙ ማምረቻዎች ዲዛይን፣ ምርትና ተከላ ለማከናወን ተዘጋጅቷል፡፡ የዘርፉ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ዳብሮ በአጠቃላይ ሀገራዊ ልማቱ ሊኖረው የሚገባ ድርሻ የማሳደግ ስራዎችም እየተከናወኑ ናቸው፡፡

ዓላማዎች

 • የኢንዱስትሪውን የፕላስቲክ ቴክኖሎጂ ደረጃ ማሳደግ፤
 • አገራዊ ልማቱን የሚያፋጥኑ የኢንጂነሪንግና የፕላስቲክ ውጤቶችን ማምረት፤
 • የአገር ውስጥ የፕላስቲክ ምርት ዓይነትና ጥራትን በማሳደግ የውጭ ገቢ ምርቶችን ማስቀረት፤

ተልዕኮ

 • ብረት ነክ ያልሆኑ የኢንጂነሪንግ ማቴሪያል ዲዛይን፣ኢንተግሬትድ በማድረግ ማምረት የሚያስችሉ የማምረቻ ቴክኖሎጂ ማልማት፣
 • የፖሊመርና የኮምፖሳይት የማምረቻ ቴክኖሎጂ ማልማት፣
 • ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸዉን፣ የገበያ ክፍተትና እጥረት የሚሞሉ ምርቶችን ማምረት፣
 •  የአቅም ግንባታ በተለይ በኮርና በክሪቲካል የሰዉ ኃይል ላይ አትኩሮ መስራት፣

የማምረቻ ፋብሪካዎች

 • የፓይፕ ማምረቻ ፋብሪካ
 • የኢንጀክሽንና በሎዉ ሞልዲንግ ማምረቻ ፋብሪካ
 • ፒቪሲ ፓይፕና ሲሊንግ ማምረቻ ፋብሪካ
 • ፖሊ ማምረቻ ፋብሪካ
 • ኮምፖሳይት ፋብሪካ
 • ፊላሜንት ዋይንዲንግ ፋብሪካ

ምርቶች

 • ፒቪሲ ፓይፖች እና ፊቲንጎች HDPE ፓይፕና ፊቲንግ         
 • ፒቪሲ ፕሮፋይል መስኮቶችና በሮች፣ ሲሊንግ
 • የኢንጀክሽንና ብሎዉ ሞልዲንግ ምርቶች
 • የኢነርጂ ሜትር አካላት,
 •  ስፕሊንክለሮች,
 • ወታደራዊ የፕላስቲክ ምርቶች
 • የኮምፖሳይት ምርቶች 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *