የመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ጉብኝት አደረገ

በመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈፃሚና ም/ስራ አስፈፃሚ የተመራ ቡድን ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በግሩፑ ስር የሚገኙትን ኢንዳስትሪዎች ተዘዋውረው ጎብኘተዋል፡፡
 
የደብረ ብርሃን የሚገኘው የኢንፍራስትራክቸር ማሽነሪ ግንባታ ኢንዱስትሪ፣የሃይቴክ ኢንዳስትሪና የሰንዳፋ ሶላር ፓኔል ማምረቻ ፋብሪካ ተጎብኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላም አጠቃላይ የተቋሙ አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በተያዘው በጀት አመት የተያዙት እቅዶች እንዲሳኩ መጠነ ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል፡፡
 
የኢጀንሲው የስራ ሃላፊዎች በቀጣይ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ እቅድን ለማሳካት የበኩላቸውን ድጋፍ በማድረግ ተወዳዳሪ የኢንጂነሪንግ ተቋም ለማድረግ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሃላፊዎችም ተቋሙን አትራፊና ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፉ ብዙ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ መንግስት እስካሁን ለተቋሙ ያደረገው ድጋፍ እንደጠበቀ ሆኖ ከዚህም በላይ አፋጣኝ ድጋፍ ለሚፈልጉ ጉዳዮች እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *