አመሰራርትና ማንነት
የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከተመሠረተ በኋላ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የራሳቸውን አወንታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችሉና የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ኢንዱትሪዎች አቋቁሟል፡፡ ከእነዚህም ኢንዱስትዎች አንዱ የሆነው የብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ከተመሠረተበት ከሐምሌ 2002 ዓ.ም ጀምሮ አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ በዘመናዊ ማሽነሪ እና በብቁ የሠው ኃይል በማሟላት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፋይዳ ያላቸው ምርቶች በማምረት ላይ ይገኛል፡፡
ከዚህ ባሻገር በዘላቂነት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅማችን ወደ ላቀ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚያስችሉ ከመንግስት እና ከህዝብ የተቀበላቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች ማለት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሮሜካኒካልና ሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸራል ሥራ፣ በደቡብ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የጣና በለስ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ግንባታ እና የዩሪ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በብቃት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው የሚመጡ ድርጅቶችን የአጋርነት ውል ስምነት በማስገባት የሥራ ዕድል በመስጠት እራሳቸውን እንዲችሉ ከማድረጉም በላይ ከቴክኖሎጂው ጋር በቅርበት በማቀራረብ ለበርካታ የሥራቸውን ሚና በኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲጫወቱ መንገድ ከመክፈቱም በላይ በሥራቸው ለብዙ ዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጥር ማድረግ የቻለ እና የሀገራችን ህዳሴ ዕውን ለማድረግ የሚተጋ ኢንዱስትሪ ነው፡፡
ተልዕኮ
- የብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ልማቱን ማፋጠን የሚያስችሉ የማምረቻ ፋብሪካዎች ዲዛይን፣ አካላትና ስርዓቶች ምርምርና ፍተሻ፣ የገጠማና ውህደት እንዲሁም ኮሚሽኒንግና የመሳሰሉትን ወሳኝ የዘርፉ ሥራዎችን ማከናወን፡፡
- ኢንዱስትሪው በተቋቋመበት ዘርፍ የኢንጂነሪንግ ማሽነሪ ፕላንቶች አመራረትና አገነባብ ፕሮዳክሽን ቴክኖሎጂ ስስተምስ በመንደፍ በዘርፉ ቴክኖሎጂ ላይ ልቆ መገኘት፡፡
- በፋብሪኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የዲዛይን፣ የተላከና የሙከራ ዓቅሞችን ለመፍጠር የሚያስችል የአመራረትና የአተገባበር ቴክኖሎጂ ሰነድ በመንደፍ አገራዊ የብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ በማልማት የሀገር አቀፍ የምርት ኔትወርኪንግ ሲስተም መገንባት፡፡
- በፋብሪኬሽን ዘርፍ ልዩ ቴክኖሎጂ የሚሹ ማሽነሪዎችን፣ ስፔሻል ኢኩፕመንት፣ ለወታደራዊ ተልዕኮ የሚጠቅሙ ምርቶችን ማምረት፡፡
- ሀገራዊ አቅማችን አሟጦ የመጠቀም ባህል በመገንባት ተመጋጋቢ የኢንጂነሪንግ መሳሪያዎች የግንባታ ዓቅም መፍጠር፡፡
ኮር ቢዝነስ
- የፋብሪኬሽን ቴክኖሎጂ በግንባር ቀደምትነት ማልማት፡፡
- የማምረቻ ፋብሪካዎች
- ፋብሪኬሽንና ስትራክቸራል ፋብሪካ
- የፎርጂንግና ፕረሲንግ ፋብሪካ
- ታወር ክሬንና ሊፍተር ፋብሪካ
- የኢንዱስትሪ ግንባታ UBM ፋብሪካ
- የጀልባ ማምረቻ ፋብሪካ
ኮር ፕላንት
- ፕሪ ፋብሪኬትድ ስቲል ስትክቸር ማምረቻ ፕላንት፣ ፓይፕ ላይን ማምረቻ ፕላንት፣ የኦክስጅን አሴቲሊን አርገን ምምረቻ ፕላንት፣ ስቲል ስትራክቸር ማምረቻ ፋብሪካ በተለይም በፋሌክሰብል ማኑፋክቸሪንግ ደረጃ ለሚመረቱ ፕላንቶች፣ የፋብሪኬሽን ኢኩፕመንት ማምረቻ ፕላንት፣ የትራንስፎርሜሽን ታወር ማምረቻ ግንባታ የሚሰራ ይሆናል፡፡
- በበጀት ዓመቱ ስቲል ስትራክቸር ማምረቻ ፋብሪካ በተለይም በፍሌክሰብል ማፋክቸሪንግ ደረጃ ለሚመረቱ ፕላንቶች ላይ አትኩሮ ይሰራል፡፡
ኮር ምርት
- ለፕላንት ግንባታ የሚሆኑ ስቲል ስትራክቸር ምርትና የተለያዩ ቤንዲንግ፣ ሮሊንግ፣ ዌልዲንግ፣ ሼሪንግ፣ ፕላዝማ ከቲንግና ኮምቢኔሽን ማሽን ምርት የሚያመርት በማንኛውም በፋብሪኬሽን የሚመረቱ ምርቶች ላይ አተኩሮ ይሰራል፡፡
- ለስኳር፣ ለማዳበሪና ለሌሎች የማምረቻ ፋብሪካዎች ግንባታ የሚሆኑ ግብዓቶችን ያመርታል፡፡
ኮር ሰርቪስ
- ከፕሪ ፋብሪኬትድ ስቲል ስትራክቸር ጋር የተያያዙ የቴክኖሎጂ ዲዛይን (Design) የምክር አገልግሎት (Consultancy) የአመራረት ቴክኖሎጂ ስልጠና (Training) ማሽን ተከላ፣ የኮሚሽኒንግና ቴስቲንግ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- በፐሪፈራል ቢዝነስ ብረታ ብረትና ፋብሪኬሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አግሮ ኢንዱስትሪ ላይ የሚሰራ ሲሆን፣ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታና ድጋፍ ላይ ያተኩራል፡፡
ፔሪፈራል ፕላንት
- የተሸከርካሪ ቦዲ ማምረቻ ፕላንት፣ የጀልባ ማምረቻ ፕላንት፣ የእርሻ ኢምፕሊመንት ማምረቻ ፕላንት፣ የዶሮ ማቀነባበሪያ ፕላት፣ ዘመናዊ ከብት እርድ ቄራ ግንባታ፣ የቆዳ ማቀነባበሪያ ፕላንት፣ ለፕላንት ግንባታ የሚሆኑ ስቲል ስትራክቸር ማምረቻ ፕላንቶችና የከተማ ቨርቲካል እርሻ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በበጀት ዓመቱ ዘመናዊ ከብት እርድቄራ ግንባ ላይ አትኩሮ ይሰራል፡፡
ፔሪፈራል ምርት
- ለሞተር ሳይክል፣ ለባይ ሳይክል፣ ስትራይ ሰይክልና ኳድራ የሚሆኑ የተሸከርካሪ ቦዲ ምርት፣ በአነስተኛ ወጪ ሊገዙ የሚችሉ ትናንሽ መኪኖች፣ ሚኒ ባሶች ለአሳ ማስገሪያ፣ ለምርት እና ለትራንስፖርት የሚያገለግሉ የጀልባ ምርት፣ የእርሻ ኢምፕልመንት ምርት
ፔሪፈራል ሰርቪስ
- በፔሪፈራል ፕላንት ግንባታ ሥራ እና በምርት ያካተተውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በዲዛይን ማማከር እና የማሰልጠን ሥራ የሚሰራ ይሆናል፡፡
ዋና ዋና ምርቶች
- ፋብሪኬሽንና ስትራክቸራል ፋብሪካ ምርቶች
- የትራክተር ትሬለሮች, የዉሃና የነዳጅ ታንከሮች , ወ.ዘ.ተ…
- የፎርጂንግና ፕረሲንግ ፋብሪካ ምርች
- የትራክተር ፍሬሞች , የተለያዩ የመስኖ ኢኩፕመንቶች …..