የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

አመሰራርትና ማንነት

በፓወር ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ልማት የሚገኝ ዕዉቀት፣ አስተሳሰብና ክህሎት ለፓወር ኢንዱስትሪ ልማትና አገልግሎት ማዋል በሚል መርህ ለሃይል ማመንጫ፣ ለሃይል ማስተላለፊያ፣ ለሃይል ማሰራጫና ቁጠባ የሚያገለግሉ ፓወር ፕላንቶች፣ ካፒታል ዕቃዎችና ላይን ማሽነሪዎችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ዲዛይን ማድረግ ፣ማምረት፣የማደስና የማሻሻል ስራ መስራት ዋነኛ ተልዕኮዉ በማድረግ ሰባት ፋብሪካዎችን አቅፎ ሰኔ 2002ዓ.ም የተቋቋመ ኢንዱስትሪ ነዉ፡፡

በሃገራችን ከተፈጠረዉ የኢኮኖሚ እድገት በመነሳት የኤሌክትሪክ ኢኩፕመንትና አክሰሰሪዎች ፍላጎት ከአቅርቦት አንፃር በኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ  ለሃይል ማመንጫ፣  ማስተላለፊያ ፣  ማሰራጫና ቁጠባ የሚያገለግሉ ፓወር ፕላንቶች፣የኤሌክትሪክ ኢኩፕመንቶችና አክሰሰሪዎች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ዲዛይን በማድረግ፣ በማምረት፣በማደስና የማሻሻል ስራ በመስራት የገበያ ክፍተትን ለመሙላት ተችሏል፡፡

ከማምረቻ ኢንዱስትዎች መስፋፋትና ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጋር ተያይዞ  የትራንስፎርመር ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ኢንዱስትሪዉ ዲስትሪቢዉሽን ትራንስፎርመሮችን ፣ፓወር ትራንስመሮችንና ስፔሻል ትራንስፎርመሮችን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እና ለተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚሰጡ ትራንስፎርመሮች ዲዛይን በማድረግ ፣በማምረትና የሪትሮፊቲንግ ስራ በመስራት ለኢንዱስትሪ ልማቱ ከፍተኛ አስተዋዕኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ የዋየርና ኬብል ማምረቻ ፋብሪካም በዓመት 12,000 ቶን የተለያዩ ዋየርና ኬብሎችን የማምረት አቅም ያለዉ ሲሆን በሃገራችን በጣም ግዙፍ የሚባልና ምርቶቹን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፣ለስኳር ፋብሪካዎች፣ለማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡርና ለበርካታ ፕሮጀክቶችና ኢንዱስትሪዎች እያቀረበ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የሶላር ሃይል ምርቶችን፣የኮምፓክት ሰብስቴሽኖችን፣ተርባይኖች፣ ፓወር ፋክተር ኮሬክተሮችንና ኢንጂኖችን በማምረት በዘርፉ ትልቅ አቅም እየፈጠረ የሚገኝ ኢንዱስትሪ ነዉ፡፡ 

ኢንዱስትሪዉ መሰረታዊ የኢንጂነሪንግ ቁመና ያለዉ ኢንዱስትሪ ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ያሉትን የማምረቻ ፋብሪካዎች ማባዛት የሚያስችል ሙሉ አቅም ገንብቷል፡፡ በዚህም መሰረት የኢንጂነሪንግና የቴክኖሎጂ አቅም ማስፋፋትና ማጎልበት የሚያስችል በአጋርነት መርህ ላይ የተመሰረተ የኢንዱስትሪ  ትስስር በመፍጠር የተሰጠዉን ተልዕኮ በቀጣይነት እንዲያሳካ አሁን የደረሰበትን እድገት መነሻ በማድረግ የሃገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን ተጨማሪ አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

 • ለሃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ ፣ማሰራጫና ለሃይል ቁጠባ የሚያገልግሉ ፕላንቶች ፣የኤሌክትሪክ ኢኩፕመንቶችና አክሰሰሪዎች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ፣ ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት፣ ሪቢዩልዲንግ ማድረግና የአፕግሬዲንግ ስራ በመስራት የገበያ ክፍተት መሙላት
 • በፓወር ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ልማት የሚገኝ ዕዉቀት፣አስተሳሰብና ክህሎት ለፓወር ኢንዱስትሪ ልማትና አገልግሎት እንዲዉል ማድረግ
 • ለኢንዱስትሪ ልማት የተመቸ ሁኔታ መፍጠር
 •  የፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ማካሄድ

ኮር ቢዝነስ

 • ፓወር ፕላንቶች፣ኤሌክትሪካል ማሽኖች ፣ኢኩፕመንቶችና አክሰሰሪዎች፡-
 •  የዲዛይንና ዴቨሎፕመንት
 • የማምረት
 • የተከላ ስራና የኮሚሽኒንግ ስራ ማካሄድ
 • ተጓዳኝ ተግባራት
 • በፓወር ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ስልጠና መስጠት
 • በፓወር ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ዙሪያ የማማከር አገልግሎት መስጠጥና መስራት

የማምረቻ ፋብሪካዎች

 • የትራንስፎርመር  ማምረቻ ፋብሪካ
 • የዋየርና ኬብል ማምረቻ ፋብሪካ
 • የፓወር ፋክተርና የኮምፓክት ሰብስቴሽን ማምረቻ ፋብሪካ
 • የኢንጂን ማምረቻ ፋብሪካ
 • የሶላር ኢነርጂ ማቴርያሎች ማምረቻ ማምረቻ
 • የሞተርና ጀኔረተር ማምረቻ ፋብሪካ
 • የተርቨባይን ማምረቻ ፋብሪካ
 • የቦይለር ማምረቻ ፋብሪካ

ምርቶች

 • ዲስትሪቢዉሽን ትራንስፎርመሮች
 •  ኮምፓክት ሰብስቴሽኖች
 • አዉቶማቲክ ፓወር ፋክተር ኮሬክተሮች
 • የዋየርና ኬብል ምርቶች
 • ኢንጂን
 • ሶላር ፓኔሎች
 • ተርባይኖች
 • ጀነሬተሮች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *