በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ኢንዱስትሪ ጉብኝት ተደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኢትዮኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኘውን የኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጎበኙ፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሕይወት ሞሲሳ(ኢንጂነር) ጉብኝቱን መርተዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል፡፡
የካሽ ሬጅስተር ማሽን ምርትን የተመለከተ ጉብኝት ሲሆን የማምረቻ ፋሲሊቲን አቅም ለመገምገም የሚረዳ መሆኑ ታውቋል፡፡
የኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሐይሉ ጫካ ባደረጉት ገለፃ በኢንዱስትሪው የሚመረተው የካሽ ሬጅስተር ማሽን በርካታ ጠቀሜታ ያሉት ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የደህንነት ጉዳይን የሚያረጋግጡ ፤የአገራችንን ቋንቋ እና የቀን አቆጣጠር የሚጠቀሙ ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *