የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የ2013 የበጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት ቀረበ

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የ2013 የበጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ቀረበ።
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከሃብት ብክነት በመላቀቀ የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የ2013 የበጀት አመት አፈጻጸም ቀርቧል፡፡
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ በኢትዮ ኢንጂነሪነግ ግሩፕ እየተካሄዱ የሚገኙ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ውጤታማ ተቋም መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ህይወት ሞሲሳ (ኢንጂነር) እንዳብራሩትም ተቋሙ የተለያዩ የሪፎርም ደረጃዎችን በማለፍ ወደ ምርታማነት ለመግባት የሚያስችለውን ጥረት እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ግሩፑ የነበረበት ቁመና የሪፎርም ስራውን ፈታኝ እንዳደረገው ያብራሩት ሃላፊዋ፣በተያዘው የበጀት አመትም የሪፍርም ስራውን በማስቀጠል ምርታማ ተቋም ለመፍጠር እንሰራለን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የቀረበ ግብረ መልስ ላይም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *