“የኢትዮጵያዊነት ቀን!”

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮያዊነት ቀን ተከበረ፡፡
መንግስት ከጳጉሜ 1 እስከ 5 ላሉት ቀናት ልዩ ልዩ መልእክቶችን በመቅረጽ ህዝባዊ እንቅስቀሴ ለመፍጠር አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 አ.ም ስለ ኢትዮጵያ ክብር በአንድነት እቆማለሁ በሚል የኢትዮጵያዊነት ቀን በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ተከብሯል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ ነው ቀኑ የተከበረው፡፡
መንግስት በሰየመው መሰረት ጳጉሜ 1 የኢትዮጵያዊነት ቀን፣ጳጉሜ 2 የአገልጋይነት ቀን፣ጳጉሜ 3 የመልካምነት ቀን፣ጳጉሜ 4 የጀግንነት ቀን፣ጳጉሜ 5 የድል ቃል ኪዳን ብስራት ቀን በመሆን ይታሰባል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *