ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ተደረገ

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት ሠራተኞች ለአገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አደረጉ፡፡ ሰራተኞቹ ባደረጉት ውይይት በአንድ አመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሠራዊቱ ድጋፍ እንዲውል በወሰኑበት ወቅት ፤ ሰራዊቱ የሕይወት መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት ሁኔታ እኛም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነታችንን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡የግሩፑ ኢንዱስትሪዎችና ዋና መስሪያ ቤት ሠራተኞች ሁለት ዙር የደም ልገሳ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይነትም ሙሉ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተጠቅሷል፡፡

https://www.facebook.com/eegroup/photos/pcb.1021882751958452/1021882675291793/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *