የዋና ሥራ አስፈፃሚ መልዕክት

ተቋማችን ኢትዮኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለሃገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነውን የአምራች ዘርፉን ለመምራትና ለመደገፍ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

በብረታ ብረት፣ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ፣ በግብርና ማሽኖች፣በአውቶሞቲቭ፣ በኮንስትራክሽን ማሽኖች እንዲሁም በፕላስቲክና ፖሊመር ምርቶች ለሃገራችን የበኩላችንን ሚና ለመወጣት እየሰራን እንገኛለን፡፡

ሃገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተደረገ ፍተሻ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ከተገኙባቸው ተቋማት ውስጥ የኛም አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ይህንን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የሪፎርም ስራ በስፋት በማከናወን ላይ እንገኛለን፡፡የተጣለብንን ተልእኮ በአግባቡ ለመወጣት እንዳንችል እንቅፋት የሆኑብንን ማነቆዎች ለመፍታት ላለፉት ሶስት አመታት ሰፊ የሪፎርም ስራዎች አከናውነናል፡፡

በነዚህ በተከናወኑት ስራዎች ተቋማችን ከድንግዝግዝ በመውጣት ብርሃን ወደ ማየትተሸጋግሯል፡፡ ከተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አንዱ መከላከያና ኮሜርሺያል የነበሩ ምርቶችን በመለየት ተቋሙ የኮሜርሺያል ምርቶች ላይ ብቻ እንዲሰማራ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
በዘልማድ የሚሰሩና የዘርፉን ተወዳዳሪነት የማይመጥኑ አሰራሮች እንደግዢ እና ሽያጭ ያሉ ስራዎች የሚመሩበት ከሃያ በላይ መመሪያዎችን ማዘጋጀትና የግልጸኝነትና የተጠያቂነት አሰራርን ለመዘርጋት እልህ አስጨራሽ ስራዎች ተከናውነዋል፣ዛሬ እያንዳንዱን ስራ በተቀመጡት አግባቦች ብቻ ለማከናወን የሚስችል ሁኔታ ለመፍጠር ችለናል፡፡ የተቋማችንን መዋቅር በማስተካከል የሰው ሃይላችንን በመመደብ በአዲስ አላማ ለተልእኮ እዲዘጋጅ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡

ለጥራት፣ ለምርምር ለስልጠና ለገበያ እና ለአይ ዘርፎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ ተቋማችንን ሪብራንድ ለማድረግ ያደረግነው ጥረትም በመንግስት ተቀባይነት አግኝቶ እነሆ ኢትዮኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለመወለድ በቅቷል፡፡ይህ ተቋማችን እያካሄደ ላለው ለውጥ ቁልፍ ሚና የሚኖረው ነው፡፡

የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት ፣የቢዝነስ ፍልስፍናችንን ጥራት ያለው፣በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት በማምረት ለደንበኞች እርካታ ቅድሚያ በመስጠት ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለንን አሰራር በመዘርጋት እየሰራን እንገኛለን፡፡
የምናመርታቸው ምርቶች ከሃገር ውስጥ ፍጆታ ባሻገር በምስራቅ አፍሪካም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ በሚመለከታቸው ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እንዲያገኙ እየሰራን ነው፡፡
ዛሬም ድረስ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሃገር ውስጥና የውጭ አጋር አካላት አብረናቸው እንድንሰራ ፍላጎታቸውን እያሳዩን በመሆኑ ዛሬም ወደ ላቀ ተልእኮ ለመነሳትና አብረን ለመስራት እንደምንችል እያረጋገጡልን ይገኛሉ፡፡ ከለየናቸው ስትራቴጂክ አጋሮቻችን ጋር አብረን እንሰራለን፡፡
በመንግሰት የተሰጠንን ተልእኮ ለመወጣትና ደንበኞቻችን ከተቋማችን የሚጠብቁት የአገልግሎት ደረጃ ለመድረስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥረት እያደረግን መሆናችንን ስገልጽ መጪው ጊዜ ብሩህ፣የጥራት፣በሁሉም እይታ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የምንችልበት መሆኑን በመተማመን ነው፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *