የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡


ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ኮምፒውተሮች ለማምረት ያለመ ነው፡፡
ድርጅቱ ለተማሪዎች፣ለመመህራንና ለተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላትን በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ለመደገፍ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በግሩፑ ስር የሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በዚሁ ዘርፍ የተደራጀ ነው፡፡
በፊርማ ስር ስርአቱ ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተመስገን ጋሮማ (ዶ/ር) እንዳሉት በተደረጉት ተከታታይ ምክክሮች እዚህ ደረጃ ላይ መድረሳችን አስደሳች ነው ብለዋል፡፡
በመቀጠል ሰምምነቱን ወደ ተግባር ምእራፍ ለመቀየር የሚያስችል ተግባር ማከናወን ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ህይወት ሞሲሳ (ኢንጂነር) በበኩላቸው ግሩፑ ራሱን ሪፎርም በማድረግ ውጤታማ ተግባር ለማከናወን እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ግሩፑ በቴክኖሎጂ ቀዳሚ በመሆን ዘርፉን የመምራት ሚናውን ለመወጣት እየሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
ከአለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ጥራት ያለውና በቂ አቅርቦት ያለው ምርት ለማምረት እየተሰራ እንደሆንም ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *