የአልጄሪያው ጂ አይ ኤስ ቢ ግሩፕ በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጉብኝት አካሄደ

ጂ አይ ኤስ ቢ በኢነርጂ፣ በኬብል፣በትራንስፎርመር ምርት፣በፕላስቲክ፣በሶላርና በልዩ ልዩ ዘርፎች ላይ የተሰማራ ነው፡፡ኩባንያው በዘርፉ የረጅም አመት ልምድ ያለውን ምርቱን ለአፍሪካና ለአውሮፓ ገበያ እያቀረበ ይገኛል፡፡የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስራ ሃላፊዎች ለአልጄሪያውያን ባለሃብቶቹ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህይወት ሞሲሳ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡በሃገራችንና በግሩፑ ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጮችና በትብብር ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ለመስራት እየተካሄደ ያለውን ተግባር አብራርተዋል፡፡የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ ኢኢግ የተሰማራባቸውን የአውቶሞቲቭ፣የግብርና ፣የኮንስትራክሽን ዘርፎች፣የብረታ ብረት፣ የፕላስቲክና ኮምፖዛይት እንዲሁም የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፎችን አብራርተዋል፡፡የአልጄሪያኑ ባለሃብቶችም ስለ ተሰማሩባቸው ዘርፎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪና በሞጆ ዋየርና ኬብል ፋብሪካዎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡በቀጣይ ሳምንት ሌሎች ኢንዱስትሪዎችንም የሚጎበኙ ሲሆን ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ጋርም የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

https://www.facebook.com/eegroup/photos/pcb.1028678044612256/1028677797945614

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *