የሰራተኛ ማህበር ተመሰረተ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ተመሰረተ፡፡በግሩፑ ህጋዊ ሰውነት ያለው ጠንካራ መሰረታዊ ማህበር እንዲመሰረት ሰፊ እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፈደሬሽን አመቻችነት በተካሄደ ጉባኤ የግሩፑ መሰረታዊ ማህበር ተመስርቷል፡፡ይህ መሰረታዊ ማህበር 11 ስራ አስፈጻሚ አባላት ያሉትና 3 አባላትን ያካተተ የኦዲት ኮሚቴ አለው፡፡ከግሩፑ የሚደረጉ ማናቸውንም ግንኙነቶችን የሚፈጽም እንደሆነ የኢሰማኮ ም/ል ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው አህመድ ነግረውናል፡፡በየኢንዱስትሪው የነበሩት ማህበራት የዘርፍ ማህበራት ሆነው እንደሚቀጥሉና ከኢንዱስትሪው ጋር የሚሰሩ ናቸው ብለውናል፡፡በዛሬው ጉባኤ ላይ መሰረታዊ ማህበሩ ህገ ማህበሩን አጽድቋል፡፡በጉባኤው መክፈቻ ላይ የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሌ ባደረጉት ንግግር በግሩፑ ውስጥ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጠንካራ የሰራተኛ ማህበር መመስረት ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት አብራርተዋል፡፡የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሕይወት ሞሲሳ (ኢንጂነር) በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር አንድነት የጥንካሬ ምንጭ በመሆኑ ማህበራቱ ወደ አንድ ለመምጣት ያደረጉትን ጥረት በማድነቅ ግሩፑም ማሕበሩን በሁሉም ዘርፍ ለማገዝና ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *