“ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” የፊርማ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ

መስከረም 12, 2014 ዓ/ም በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ “የነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” የፊርማ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡በዛሬው እለት በተካሄደው መርሀ ግብር የዘጠኙ ኢንዱስትሪዎችና የዋና መስሪያ ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሕይወት ሞሲሳ (ኢንጂነር) ሁላችንም በአንድነት በመቆም ለአገራችን ድምፅ መሆን ይገባናል ብለዋል፡፡በአገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አገራት የአገራችንን ታሪክ ካለመገንዘብ የሚፈፅሙት ተግባር ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ የራሷ ባህልና ታሪክ ያላት የነጻነት ተምሳሌት መሆኗንም አስረድተዋል፡፡በመሆኑም ከአባቶቻችን የወረስነውን ነጻነት ለልጆቻችን ማስረከብ እንዳለብን ተናግረዋል፡፡ፖለቲካዊ አንድነታችንን በመጠበቅና ኢኮኖሚያችንን በማሳደግ ከውጪ ጥገኝነት ለመላቀቅ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በአገራችን እየተካሄደ በሚገኘው የህልውና ዘመቻ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

https://www.facebook.com/eegroup/photos/pcb.1030897977723596/1030897901056937

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *