ጂ አይ ኤስ ቢ ግሩፕ ከኢኢግ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ

የአልጄሪያው ጂ አይ ኤስ ቢ ግሩፕ ሃላፊዎች ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስራ ሃላፊዎች ጋር በዋናው መስሪያ ቤት ተወያዩ፡፡
በዛሬው እለት በተደረገው ምክክር ባለሃብቶቹ በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የእውቀት ሽግግር ለማድረግ በተለይም በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ያለውን የማምረቻ ፋሲሊቲ በማሳደግና ስትራቴጂክ የሆኑ ምርቶችን በጋራ ለማምረት ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡
የግሩፑ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቴክኖሎጂ፣በክህሎትና በካፒታል ታግዞ ምርታማነቱን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል፡
የአለም ገበያ እየሰፋ መምጣቱን ያወሱት ሃላፊው በብዛትና በጥራት ተፈላጊ ምርችን ማምረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡ለዚህም ከአልጄሪያው ጂ አይ ኤስ ቢ ግሩፕ ጋር በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ በመግለጽ፡፡
ባለሃብቶቹ ዛሬ ያደረጉት ውይይት በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ተዛዋውረው ከጎበኙ በኋላ ነው፡፡
ከዚም በተጨማሪ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን፣ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ከሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *