የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉብኝት በአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ቀጥሎ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉብኝት በዛሬው እለት በአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ቀጥሎ ተካሂዷል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በመሆን ነው ጉብኝቱን እያደረጉ የሚገኙት፡፡
በዚሁ ወቅት የኢንዱስትሪው ተወካይ ሃላፊ አቶ እያሱ ኢንዱስትሪው ስለሚገኝበት ተጨባጭ ሁናቴ፣ተስፋቸውንና ስጋቶቹን ጨምረው አብራርተዋል፡፡
የኢንዱስትሪው የማኔጅመንት አባላት ትኩረት ይሻሉ ያሏቸውን ሃሳቦች አንስተዋል፡፡
በዋነኛነት የንብረት ስርቆት፣የብራንድ ልየታ፣የደንበኛ አያያዝ ጉዳዮች በትኩረት ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው አምባደር ምስጋኑ ጥራት ያላቸውን ብራንዶች ላይ ብቻ በመለየት በቀጣይ የሚሰራ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ለንብረት አያያዝ ተገቢውን ትኩረት በመስጠትና በቴክኖሎጂም ጭምር በማገዝ መሰራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በኦፕሬሽንና በሃብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችም ገለጻና ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *