ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ዩቶንግ ኩባንያ ውይይት አካሄዱ

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ዩቶንግ ኩባንያ በቀጣይ ሊኖራቸው በሚገባ ግንኙነት ላይ ወይይት አካሄዱ፡፡
የኩባንያው ተወካዮች በግሩፑ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ነው ውይይት ያካሄዱት፡፡
ተወካዮቹ ዩቶንግ ኩባንያ በግሩፑ ስር ከሚገኘው ከቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር ባለፉት 10 አመታት ያከናወናቸው ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡
ላለፉት 10 አመታት ገደማ ጠንካራ ግንኙነት መመስረታቸውንና ይህንን ግንኙነታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ግንኙነቱ በሃገር ወስጥ ገበያ ብቻ ሳይገደብ በአፍሪካም የዩቶንግ ምርትን መዳረሻ ለማድረግ ኢትዮጵያ ተመራጭ በመሆኗ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በቀጣይ የተጠናከረ ግንኙነት ለመመስረት ፍላጎቱ እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአፍሪካ መቀመጫና የዲፕሎማሲ ማእከል በመሆኗ የአፍሪካን ገበያ ለማዳረስ አመቺ ሃገር መሆኗን አንስተዋል፡፡
በቀጣይ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣትና ለጥራት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ጭምር ግንኙነቱን አሁን ካለበት ደረጃ በመሰረቱ ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
የአጋርነት ደረጃው የሚገኝበትን ሁናቴ በዝርዝር በመፈተሸ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ በማስታወስ፡፡
የግሩፑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸው ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለመታጠቅ ከኩባንያው ጋር በቅርበት መሰራት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡
በቀጣይ የግንኙነት አግባቡን ሊያሳድጉ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *