ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የጣሊያኑ ፋሪሰን ኩባንያ ውይይት አካሄዱ፡፡
ፋሪሰን ኩባንያ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ግንባታ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ነው፡፡
በግሩፑ ስር ከሚገኘው ከኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር የተለያዩ ስራዎችን ያከናወነ የቆየ ሲሆን በተለይ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው ፋብሪካ ላይ የጀመረውን የማምረቻ ፋሲሊቲ ስራ ለማጠናቀቅ በቅርቡ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በዛሬው ውይይት በመጪው ግንቦት ወር ላይ በመምጣት ወደ ስራ በሚገባበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በደብረ ብርሃን የሚገኘውን የማምረቻ ፋሲሊቲ አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባቱ ለሃገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ነው፡፡
የስራው መጠናቀቅ ስካፎልዲንግና ፎርም ዎርክን በማምረት የሃገሪቱን የግንባታው ዘርፍ ለማሳደግም ወሳኝነት አለው፡፡
ዘርፉ ከፍተኛ የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ስራው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ፍላጎት እንዳለ ነው የተገለጸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሁለቱ ተቋማት መካከል ፓርትነር ሺፕ በመመስረት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ምክክር ተካሂዷል፡፡
የባለሙያዎች ስልጠናና የቴክኖሎጂ ሽግግር በስራ ሂደቱ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡
በቀጣይ የሚከናወኑት ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ በመጪው ግንቦት ወር ውይይት እንዲደረግበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
