በኢትዮ- ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሀብት ምዝገባ ስልጠና መርሃ ግብር ተካሄደ ፡
በዛሬው እለት በዋናው መስሪያ ቤት ይህን ዘመናዊ የሀብት ምዝገባ ለመከወን የሚያስችል ስልጠና ተካሂዷል።
የኢ/ኢ/ግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በመክፈቻው ላይ ”ሰዎች ባገለገሉበት ጊዜ የሚገነቡት ስብዕና ትልቅ ነው” ብለዋል፡፡በመሆኑም ስነ ምግባሩ የጠራ አመራር ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የተቋማችንን ገጽታ ለመገንባት እና ሙስናን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ግልጽና የጠራ አሰራርን መዘርጋት በመሆኑ ይህንን ዲጂታል የሀብት ምዝገባ ሰራ ማኔጅመንቱ አርአያ በመሆን ሊተገብረው እንደሚገባ ተናግረዋል።
ይህ ዘመናዊ የሀብት ምዝገባ ስልጠና ለማኔጅመንት አባላት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ለሁሉም ሰራተኞች ይቀጥላል።
በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ የግሩፑ የስነ ምግባር አገልግሎት ሃላፊ አቶ በላይ ለገሰ እና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ሀላፊ አቶ ዘላለም በለጠ ዘመናዊ የሀብት ምዝገባ ስርአቱን ለማኔጅመንቱ በማስተዋወቅ ምዝገባውን አስጀምረዋል፡፡