በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር በሚገኘው የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ጉብኝት ተካሄደ፡፡
በጉብኝቱ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፣ የግሩፑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና አማካሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ እንዳያመርት ማነቆ በሆኑበት ጉዳዮች ላይ ውይይትና ምክክር ተካሂዷል፡፡
ከውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር በተያያዘ ግብአቶችን በሚፈለገው መጠንና ጊዜ አለማግኘት አንዱ ተግዳሮት ሆኖ የተነሳ ሲሆን ይህ የሚቀረፍበት ሁኔታ ላይ በትኩረት ምክክር ተካሂዷል፡፡
ዘመናዊ የማምረቻ ማሽነሪ አለመኖር ሌላው ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ እንዳያመርት ያደረገው ጉዳይ በመሆኑ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው አምባሳደር ምስጋኑ አርጋው ኢንዱስትሪው ምርትና ምርታማነቱን ለማስቀጠል የሚስተዋሉ የማምረቻ ማሽን እድሳትና፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር አፋጣኝ ምላሽ ተሰቶት የተጀመሩት ምርቶች ወደ ገበያ መግባት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ፋብሪካው የተለያየ መጠን ያላቸው የትራንስፎርመር ምርቶችን በማምረት የሃገሪቱ የሃይል አቅርቦት ስራ እንዲሳለጥ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዋነኛነት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምርቱን እያቀረበም ይገኛል፡፡
ጉብኝቱ በሌሎች ኢንዱስትሪዎችም በቀጣዮቹ ቀናትም እንደሚቀጥል ይጠበቃል ።
