በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የካይዘን ትግበራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የካይዘን ትግበራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡
ግምገማውን የግሩፑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴና የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምንዳዬ ይርጋ መርተውታል፡፡

በኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ድጋፍ፣ በግሩፑ የካይዘን ትግበራ ስራ ሲከናወን ቆይቷል፡፡
በዚህ መሰረት የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው እና ማሻሻል የሚጠበቅባቸው ኢንዱስትሪዎች ተለይተው ቀርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡
በተለያዩ የምዘና መስፈርቶች የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡት ኢንዱስትሪዎች ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ፣ በፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ፣ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡
ቀሪዎቹ ኢንዱስትሪዎች ፈጥነው በመስራት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ጋር ውሎ ተገብቶ እየተሰራ ያለው ስራ እና በጋራ እየተከናወነ ያለው ስራ የሚጠናቀቀው በተያዘው የበጀት አመት መጨረሻ ነው፡፡
የግሩፑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ በተያዘው የበጀት አመት ቀሪ ጊዜ ኢንዱስትሪዎች የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መትጋት ይኖርባቸዋል፡፡
የአመራሩ ቁርጠኝነት መጨመር ፣ለስራዊ አስፈላጊውን በጀት መመደብና የስቴሪንግ ኮሚቴው ፈጣን እንቅስቃሴ ውጤቱን ለማሳደግ እንደሚያስችል ነው ኢንጂነር እንዳወቅ የገለጹት፡፡
በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ አጠቃላይ ግምገማ የሚደረግ ሲሆን ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ጋር በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት እንደሚደረግ ይጠበቃል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *