የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት እንደቀጠለ ነው፡፡

በዛሬው እለት ለኮንስትራክሽን፣ለስኳር፣ለሲሚንቶ፣ለትራንስፖርትና ለሌሎችም ዘርፎች መለዋወጫ በማቅረብ ላይ የሚገኘው የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተጎብኝቷል፡፡
የኢንዱስትሪው አፈጻጸሞችና ቁልፍ ችግሮች ቀርበው ውይይት ተካሄዶባቸዋል፡፡
በውይይቱ ኢንዱስትሪው ለአምራች ኢንዱስትሪዎች መለዋወጫዎችን በማቅረብ ዘርፉን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡
የዘመናዊ ማሽነሪ እጥረት እና ግብአት ቁልፍ ችግሮች በሚል በኢንዱስትሪው የተለዩ ናቸው፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ኢንዱስትሪው በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገቡ መለዋወጫዎች በሃገር ውስጥ እንዲመረቱ የማድረግ አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ቁልፍ ችግሮችን በመለየት መፍታት ይገባል ብለዋል፡፡
የማምረት አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም አመራሩና ሰራተኛው መትጋት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ሃገራዊ የመንግስት የልማት እቅዶችና ውጥኖችን ለማሳካት የሚያግዙ ምርቶች እንዲመረቱ ከዚህም በላይ መንቀሳቀስ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
አለም አቀፉ የገበያ ውድድር እያደገ በመሆኑ የገበያ ሚዛኑን ለማስጠበቅ እንደ አቃቂ ያሉ የሃገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሚና መጎልበት እንዳለበት ምክክር ተደርጓል፡፡
ለስኬታማነቱም ከግሩፑ ጋር እየሰሩ የሚገኙ በየደረጃው የሚገኙ ባለ ድርሻ አካላትን በማሳተፍ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡18:15

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *