የውስጥ ኦዲትን በመተግበር የግሩፑን አሰራር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ

የውስጥ ኦዲትን በመተግበር የግሩፑን አሰራር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ፡፡ትላንት እሮብ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም በውስጥ ኦዲት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡በዚሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ የማኔጅመንት አባላት ፣የስታፍ አመራሮችና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል ።የውስጥ ኦዲት አገልግሎት በፋይናንስ፣ በአፈፃፀምና በህጋዊ አሰራር ላይ በማተኮር እንደሚሰራ ተዳሷል።በግሩፑ የወጡ አሰራሮች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ስለመከበራቸው ክትትል ማድረግ የውስጥ ኦዲት አንዱ ተግባር መሆኑም ውይይቱ ተደርጎበታል፡፡የተቋሙ የውስጥ ኦዲት አሰራርን በማጠናከር ክፍተቶችና ጉድለቶች እንዲታረሙና፤ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተብራርቷል፡፡የግሩፑ የኦዲት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ዘመን አርፍጮ እንዳብራሩት ግሩፑ በተለይ ከሪፎርሙ አመታት በፊት የተቋሙ የውስጥ ኦዲት ያልተጠናከረ በመሆኑ ለሃብት ብክነት እና ለብልሹ አሰራር ተዳርጎ ቆይቷል፡፡ይህንን አሰራር በመቀየር መደጋገፍን መሰረት ያደረገ የውስጥ ኦዲት አሰራር ለመዘርጋት ጥረቶች እየተደረጉ በመሆናቸው ሁሉም ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ቅንጅታዊ አሰራር እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ እንዳለበት አብራርተዋል፡፡የውስጥ ኦዲት አገልግሎት የአመራር አጋዥ፣በስራ ላይ እሴት የሚጨመርና ተቋሙን ወደ ተሻለ ከፍታ የሚያደርስ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *