የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች በፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘውን የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች በፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘውን የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኙ፡፡
ፋብሪካው የትራንስፎርመር ምርት በማምረት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ለተለያዩ ደንበኞች እያቀረበ ይገኛል፡፡
የተሻለ የጥሬ እቃ አቅርቦት ያገኘ በመሆኑ ሰራተኞች ሰፊ የሆነ የማምረት እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዳሉት ፋብሪካው በአቅርቦትና በጥራት ከዚህም በተሻለ በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅበታል፡፡
ፋብሪካው የሃገሪቱን የሃይል ዘርፍ መደገፍ የሚችል አቅም እንዳለውም አስታውሰዋል፡፡
ምቹ የስራ ከባቢን ለሰራተኞች በመፍጠር ለተሻለ ውጤት መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የፋብሪካውን ቁልፍ ችግሮች ግሩፑ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑም በጉብኝቱ ወቅት አንስተዋል፡፡
በጉብኝቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡19:41

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *