እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሳችሁ!

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና በአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በልዩ ልዩ ሁነቶች ተከበረ።
በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” እንዲሁም በአለም አቀፍ ለ112 ጊዜ “INNOVATION AND TECHNOLOGY FOR GENDER EQUALITY” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አመራርና ሰራተኞች እለቱን በፓናል ውይይት፣ በተለያዩ አዝናኝ የኪነጥበብ ፕሮግራሞች እንዲሁም የላቀ አፈፃፀም ላላቸው ሴት ሰራተኞች የማበረታቻ ሰርተፊኬት በመስጠት አክብረዋል።
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ ሴትን ማክበር የዘመናዊነት መገለጫ በመሆኑ የሴቶችን እኩልነት በተግባር ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል።
በኢንዱስትሪው ከ48 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች በመሆናቸው የኢንዱስትሪውን የህፃናት መዋያ፣ ትምህርት ቤት እንዲሁም ጤና ጣቢያ በአዲስ መልኩ እንደሚደራጅ ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የግሩፑ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ተወካይ ሀላፊ ወ/ት በረከት አሰፋ በበኩላቸው ቀኑ የሴቶችን እኩልነት ለማስፈን ያለመ መሆኑን በማንሳት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በተመሳሳይ በአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪም ቀኑ የተከበረ ሲሆን የተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከብሯል።
በእለቱም በኢንዱስትሪው የሚገኘውን ተስፋ የህፃናት መዋያ በአዲስና መልክ ተደራጅቶና ለልጆች ምቹ እንዲሆን ተደርጎ ተመርቆ ተከፍቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *