ኢግዚብሽኑ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እየተሳተፈበት የሚገኘው አለም አቀፍ ፎረም አካል ነው፡፡
ከመላው አለም የተውጣጡ ከ600 በላይ የንግድ ተቋማት እየተሳተፉበት የሚገኘው ፎረም የተጀመረው በትላንትናው እለት ነው፡፡
ዛሬ በተከፈተው ኢግዚብሽን ላይ ክልሎች ያሏቸውን የኢንቨስትመንት አቅምን ጨምሮ ልዩ ልዩ ተቋማት ያላቸውን አቅም እያሳዩ ነው፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕም ምርትና አገልግሎቱን የሚያስተዋውቁ ስራዎቹን ለተሳታፊዎች እያስጎበኘ ይገኛል፡፡
በፎረሙ በሁለተኛ ቀን ውሎ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ስኬቶችና እድሎች ላይ በማተኮር ሲካሄደ የዋለ ሲሆን በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
