በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የውስጥ ኦዲት ስራን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡
በውይይቱ ተቋሙ የወስጥ ቁጥጥር ስርአቱን ለማጠናከር የግሩፑ የኦዲት አገልግሎት ባቀረበው ግኝቶች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
የ2015 የ9 ወራት የፋይናንሺያል ኦዲት ግኝቶች ቀርበዋል፡፡
እንዲሁም የፐርፎርማንስና ኮምሊያንስ ኦዲት ግኝቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በውይይቱ እንደተነሳው ግሩፑ የያዛቸው እቅዶች ከግብ እንዲደርሱ የውስጥ ቁጥጥር ስርአቱ መጠናከር አለበት፡፡
ክፍተቶች ከስር ከስር እየታረሙ መሄዳቸው ለግሩፑ ሁለንተናዊ ውጤታማነት አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል፡፡
ሆኖም በዘርፉ በቂ እና ብቁ የሆነ የሰው ሃይል አለመኖር፣በቴክኖሎጂ አለመዘመን ስርአቱን በሚታሰበው ደረጃ ለመዘርጋት ችግር ተብለው የተያዙ ናቸው፡፡
ችግሮቹ በስልጠና ፣በአደረጃጀት እና በቴክኖሎጂ ዝርጋታ በመፈታት ላይ እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡
የቀረበው የኦዲት ግኝት ላይ ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ግብረ መልስ ለመስጠት ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
የኢንዱስትሪ ዋናና ም/ል ዋና ስራ አስኪያጆች፣ የፋይናንስ፣ የፕላኒንንግ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዚህ ምክክር መድረክ የ2016 በጀት አመት እቅድ የትኩረት መስኮች ላይም ምክክር ተካሂዷል፡፡
ውይይቱን የመረቱት የዋና ስራ አስፈጻሚ አሲስታንስ ጽ/ቤት ሃላፊ ጤና ግዛው(ዶ/ር) እንዳብራሩት እቅዱ ሲዘጋጅ በተለይም የውስጥ አቅምን አሟጦ ማቀድን፣አሳታፊነትን፣የመረጃ ግልጸኝነትን፣የፕሮጀክት ስራዎች ላይና የኢንዱስትሪዎች ትስስርን በተለየ ትኩረት እንዲደረግባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
