ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከቤላሩሱ ኢፕቲችያ ጀነራል ትሬዲንግ (ኢ.ጂ.ቲ. ) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከቤላሩሱ ኢፕቲችያ ጀነራል ትሬዲንግ (ኢ.ጂ.ቲ. ) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ የግብርና ማሽነሪዎችን ለማቅረብ የሚያስችላቸው ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ገበያ በተጨማሪ ለምስራቅ አፍሪካ ገበያ ጭምር የግብርና ማሽነሪዎችን ማቅረብንም ያካተተ ስምምነት ነው፡፡
በቤላሩስ እውቅና ያለው ኢጂቲ ኩባንያ ከግሩፑ ጋር በግብርና ማሽሪዎች ኦፕሬሽን ስራዎች፣በቴክኒክ፣በፋይናንስና በመረጃ ስራዎች ከግሩፑ ጋር በጋራ ይሰራል፡፡
በግሩፑ የማምረቻ ፋሲሊቲዎችን በመትከል ትራክተር፣ተሸከርካሪዎች፣የውሃ ፓምፕ፣ጄኔተርና ሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶችን ማምረት የሚቻልበት ሁኔታ በስምምነቱ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡
የግሩፑ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ፣የቴክኒክ ስልጠናና የልምድ ለውውጥ የሚያገኙበት አሰራር ይዘረጋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ ከተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በጋራ የሚሰራበትን ምክክሮች እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *