ሁለቱ ተቋማት የመንገድ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክት መስቀያ ምሰሶ (Sign post)፣ የመንገድ አቅጣጫ ጠቋሚ እና የቤት ቁጥር ታፔላዎችን የማምረት፣የማጓጓዝና የመትከል ስራ ውል ፈጽመው ነው እየሰሩ የሚገኙት፡፡
እንቅስቃሴው የአዲስ አበባ ከተማን ለማዘመን በሚደረገው እንቅስቃሴ በተመረጡ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የአድራሻ ታፔላ ለመስራት፣ ለማጓጓዝና ለመትከል የሚያስችል ስራ ነው። በቀጣይም በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ለመስራት የሚያስችል ምክክር አድርገዋል።
በስምምነቱ መሰረት በአጠቃላይ ሰርቶ ለማስረክብ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ ተገልጿል።


