የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋናው መስሪያ ቤት፣አዲስ ማሽን መለዋወጫና ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና ኢትዮ ፕላስቲክ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በጋራ በመሆን በዛሬው እለት በአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የችግኝ መትከል መርሃግብር አካሂደዋል።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ “በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ይገኛል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን በተፈጥሮ አየር መዛባት ተጎጂ መሆኗን ጠቅሰው ይህን ጉዳት መልሶ ለመንባት ዛሬ የተተከሉ ችግኞች ለትውልድ የሚተላለፉ በመሆናቸው በቀጣይ በማስፋፋት ጠንክረን ሀገራችንን መገንባት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል። በመልዕክታቸውም አረንጓዴ አሻራችንን በማሳረፍ የዜግነት ግዴታችንን መወጣት እንዳለብን አስገንዝበዋል።
በመርሃግብሩ የግሩፑ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ጨምሮ የፀጥታ አካላትም ተሳትፈዋል።














