የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚና የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ለነበሩት ወ/ሮ መሰረት ደስታ የሽኝት መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

ወ/ሮ መሰረት በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ድኤታ በመሆን መሾማቸውን ተከትሎ ነው መርሃ ግብሩ የተካሄደው፡፡
በሸራተን አዲስ የተካሄደው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የግሩፑ የስራ አመራር ቦርድ ፣ የማኔጅመንት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
ሃላፊዋ በተቋማችን በነበራቸው ቆይታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የግሩፓችን የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት አቶ አየለ ከበደ ፣ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ እና ሌሎች ታዳሚዎች ወ/ሮ መሰረት በተቀቋማችን በነበሩበት ወቅት ላሳዩት ትጋት፣ታማኝነት ቁርጠኝት ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ መልካም እድል እንዲገጥማቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ወ/ሮ መሰረት በበኩላቸው ሃገራቸውን በዚህ ከፍ ባለ ደረጃ እንዲያገለግሉ እድሉን ያመቻቸላቸውን መንግስትን ያመሰገኑ ሲሆን በግሩፑ አብረዋቸው ሲሰሩ የነበሩትንም በሙሉ አመሰግነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *