በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላት  በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ።

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣
በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መሀመድ አብዱ ለተመራው ቡድን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
‘ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከየት ወደ የት’ በሚል ርዕስ ጽሁፍም የቀረበ ሲሆን ግሩፑን ለመለወጥ የተደረጉ ሁለንተናዊ ጥረቶች፣የተገኙ ስኬቶች እና የቀጠሉ ተግዳሮቶች ላይ ገለፃ ቀርቧል፡፡
የውጭ ምንዛሬ እጥረትና የጥሬ እቃ እጥረት ባላበት ወቅትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከኪሳራ በመውጣት ትርፍ ማስመዝገቡ ቀርቧል፡፡
ከገለት በኋላ በፖወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘውን የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ እንዲሁም አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተጎብኝቷል።
የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ላይ የትራንስፎርመር አመራረት ሂደት ላይ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡በሙሉ አቅም በማምረት ረገድ ያሉ ተግዳሮቶች ለአባላቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
በአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በተመሳሳይ የምርት እንቅስቃሴ እና የማሽኖችን አቅም ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በነገው እለት በሌሎች ኢንዱስትሪዎች ጉብኝቱ ተደርጎ የማጠቃለያ ውይይት ይካሄዳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *