አዲስ አበባ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ባለሙያዎች ጉብኝት አደረጉ።
የጉብኝቱ ዋና አለማ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ (ትራንስሚሽን) ታወሮችን ለማምረት በግሩፑ ተቋማት ጋር ስምምነት ለማድረግ ኢንዱስትሪዎቹ ያላቸውን አቅሞች፣ ማለትም የማምረት አቅም፣የምርት ጥራት እና ፍጥነትን ለመመልከት ታላሚ ያደረገ ጉብኝት ነበር።
ይህ ጉብኝት በኢንዱስትሪው ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በሌሎችም የግሩፑ ኢንዱስትሪዎች ጉብኝት እየተደረገ መሆኑን እና ግሩፑ ያሉትን ኢንዱስትሪዎች አቅም በማስተሳሰር ስራውን ለመስራት ያለውን አቅም ለማመላከት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
በግሩፑ ስር የሚገኙትን ኢንዱስትሪዎች ጉብኝታቸውን እንዳጠናቀቁ ስምምነት ላይ ከተደረሰ የኤሌክትሪክ ትራስሚሽም አውታሮችን ለማምረት ከግሩፑ ኢንዱስትሪዎች ጋር ስምምነት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።













