በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የአድራሻ ታፔላ ለማምረት በተስማሙት መሰረት ስራዎች እየተካሄዱ ነው፡፡

ሁለቱ ተቋማት የመንገድ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክት መስቀያ ምሰሶ (Sign post)፣ የመንገድ አቅጣጫ ጠቋሚ እና የቤት ቁጥር ታፔላዎችን የማምረት፣የማጓጓዝና የመትከል ስራ ውል ፈጽመው ነው እየሰሩ የሚገኙት፡፡
እንቅስቃሴው የአዲስ አበባ ከተማን ለማዘመን በሚደረገው እንቅስቃሴ በተመረጡ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የአድራሻ ታፔላ ለመስራት፣ ለማጓጓዝና ለመትከል የሚያስችል ስራ ነው። በቀጣይም በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ለመስራት የሚያስችል ምክክር አድርገዋል።
በስምምነቱ መሰረት በአጠቃላይ ሰርቶ ለማስረክብ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *