ኤግዚብሽን ተከፈተ::በአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ከህዳር 02-06/2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ኤግዚብሽን ዛሬ ተከፈተ:: በኤግዚብሽን ማዕከል ለስድስት ቀናት ለዕይታ ክፍት ሆኖ የሚቆየዉ ይህ ኤግዚብሽን በሞተር ተሽከርካሪዎችና መለዋወጫዎች፣ በግብርና እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ::ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሞተርና ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዘርፍ ላይ የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶች ይዞ በመቅረብ በኤግዚብሽኑ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል::