ጥር 01/2016 ዓ.ም:-ኢኢግ
በዛሬው እለት የዋናው መስሪያ ቤት እንዱሁም የዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች የሀብት አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዋና ዋና ስራዎች ላይ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ግሩፑ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ እና ትርፋማነቱን ለመጨመር የሚያስችለው አዲስ አደረጃጀት ተግባራዊ በማድረግ እየሰራ የሚገኘው የሰው ሃይል ምደባ አፈጻጸም ተገምግሟል፡፡የሰው ሀብት ምደባውን በተያዘው ሳምንት ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ግልፅ የሆነ የምደባ ሪፖርት እንዲቀርብ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ግሩፑ በመንግስት የሚጠበቅበትን ግብር መክፈል እንደሚጠበቅበት ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ከግብር አከፋፈል አንፃር ግልፅ እና የተሟላ ሪፖርት በሁሉም ኢንዱስትሪዎች ለቀጣይ ተሟልቶ እንዲቀርብ ምክክር ተካሂዶበታል፡፡
የይዞታ ጉዳይ ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ተሰቶት እንዲሰራ፣ከፋይናንስ አኳያ የተሟላና ግልፅ ሪፖርት እንዲዘጋጅ፣ንብረትን ለይቶ በማወቅ ወደ ገንዘብ እንዲለወጥ መስራት እንደሚገባ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የንብረት ኪራይ የውል መመሪያ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የሀብት ልየታ እና ምዝገባ ስራን ማጠናቀቅ፣ የንብረት አጠቃቀም ፣ የሂሳብ መዝገብን ወቅታዊ ማድረግ ፣አሰራርን ከማዘመን አንፃር የግዥ ስርአትን በቴክኖሎጂ ማገዝ በስፋት ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
የወጪ ቅነሳ ማጠናከር እና የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በእቅድ መምራት ይገባል ተብሏል፡፡ የውጭ ምንዛሬ ችግር ለመፍታት በሚያስችል መልኩ የግብአት አማራጮች መፈለግ ላይ መስራት እንደሚገባ፣ አማራጭ ገቢ ማሰገኛ ዘዴዎች ላይ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
ያሉትን ሃብቶች ከብክነት በመታደግ ወደ ገቢ እና ምርት እንዲገቡ በማስቻል የግሩፑን ውጤታማነተ ለማሳደግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡