በግሩፑ ስር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በኦፕሬሽን ስራዎች፣በሃብት አስተዳደርና በሪፎርም ስራዎች ያከናወኗቸው አፈጻጸሞች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተካሄዶባቸዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን የውጭ ምንዛሪ እና የግብአት እጥረት ተቋቁመው የውስጥ አቅማቸውን አሟጠው በሰሩት ስራ ግሩፑ በስድስት ወራት ውስጥ 131 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ቀርቧል፡፡
በበጀት አመቱ መጀመሪያ ግሩፑ የተለጠጠ እቅድ ይዞ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም የግብአት እጥረት የታቀደውን ያክል ትርፍ እንዳያስመዘግብ ማድረጉም ቀርቧል፡፡
በሪፎርም ስራዎችም ግሩፑ አዲስ አደረጃጀት ለመዘርጋት ፣የስልጠና ማእከል ለማቋቋም እና የኢ አር ፒ ስራዎችን ለመተግበር የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም ላይም ማናጅመንቱ ተወያይቷል፡፡
ግሩፑ በጥራት ስራ አመራር ስራዎች ምርትንና የአሰራር ስርአትን ሰርቲፋይ ለማስደረግ ያከናወናቸው ተግባራትም ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የተጀመሩ ስራዎችን ከዳር በማድረስ የግብአት እጥረትን ለመቀነስ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
ለሁለተኛ ግማሽ አመት ብክነትን በመቀነስ፣ወጪ ቆጣቢ ሆኖ በመስራት፣የውስጥ አቅምን አሟጦ በመጠቀም እና የእቅድ ክለሳ በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት እንደሚገባም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡