በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኘውን የብረታብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
በእለቱም የብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ አለማር ስለ ተቋሙ ያለውን አቅምና ነበራዊ ሁኔታ ለአመራሮቹ ገለፃ አድርገዋል፤ አመራሮቹም ከኢንዱስትሪው ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡እንዲሁም በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ የተሰሩ ስራዎችንና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡