ለኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት የኮርፖሬት ገቨርናንስና የፋይናንስ ስርአት የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው የተዘጋጀው በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ነው፡፡
በመክፈቻው ላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የስርአት ግንባታ ዘርፍ ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ እንዳሉት በግሩፑ ባለፉት አመታት በተከናወነው የሪፎርም ስራ የነበረውን ከፍተኛ የሃብት ብክነት ማስቆም ተችሏል፡፡
ወቅቱን የጠበቀ፣መንግስትና ህዝብ የሚጠብቁት ደረጃ ላይ ለመድረስ ከዚህም በላይ ተግባራት ማከናወን እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡


የአስተዳደሩ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ስርአት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መጠሪያሽ ኃይለጊዮርጊስ በሰጡት ስልጠና ላይ እንደገለጹት ለግሩፑ ውጤታማነት የአስተዳደራቸው፣የግሩፑ የስራ አመራር ቦርድና የማኔጅመንቱ የሶስትዮሽ ጥምረት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡


ግሩፑን ዘመናዊና ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያችሉ የኮርፖሬት ገቨርናንስ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ለግሩፑ ሁለንተናዊ ለውጥ ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በአስተዳደሩ፣በቦርዱና በማኔጅመንቱ መካከል ያለው መደጋገፍ ከፍተኛ በመሆኑ ግሩፑን የሚጠበቅበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *