በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክት አፈፃጸም ላይ ግምገማ ተከናወነ፡፡

ግንቦት 13/2016 ዓ.ም (ኢ.ኢ.ግ)
የግሩፑ ኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስር ባለው የፕሮጀክት አሹራንስ ዲቪዥን አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክት  አፈፃጸም ላይ ግምገማ  አከናውኗል፡፡
ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ለማዘመን የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ዝርጋታን ለማከናወን ወደ ስራ የገባ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ  ፌዝ የፕሮጀክት አፈፃጸም ላይ በመድረስ ወደ ሁለተኛ ፌዝ የመረጃ ስርዓት ንድፍ ሂደት ተጀምሯል፡፡ 
የግምገማው ዋና አላማ በተያዘው ጊዜና በጀት ውስጥ የታቀደው ፕሮጀክት የደረሰበትን የአፈፃጸም ደረጃ ተግባራዊነቱን በጋራ ለማረጋገጥ፣ የታዩ ችግሮችን በመለየት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ መነሻ በማድረግ ወደ ስራ ለመግባት  የታለመ መሆኑን የግሩፑ የኢንፎርመሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት  ኃላፊ አቶ አብደላ ሳኒ ተናግረዋል፡፡
በተያዘው እቅድ መሰረት የፕሮጀክት አፈፃጸም ሂደቱን ጠብቆ መከናወኑ እንደጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን ለስራው መጠናቀቅ ችግር የፈጠሩ ጉዳዮች እንደገና ማየትና በዋናነት የመረጃ ክፍተቶችን መሙላትና ግንዘቤ መፍጠር ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
በቀጣይም በመጀመሪያ ፌዝ ላይ የተያዘው ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ የደንበኛ ፊላጎትን በጠበቀ መልኩ እንዲጠናቀቅ ማድረግ ላይ በጋራ መስራት እንዳለባቸው መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *