በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋናው መ/ቤት የብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ፡፡

4/2/2017 ዓ.ም (ኢ.ኢ.ግ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ “ሰንደቅ አላማችን ለብሄራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው የብሄራዊ ሰንደቅ አላማ ቀን የግሩፑ  አመራሮች እና ሰራተኞች ብሄራዊ መዝሙር በጋራ በመዘመር አክብረዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ መሐመድ አባሚልኪ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ያላትን ከፍታ ለማደስ በሚደረገው ርብብርብ  ግሩፓችንም የራሱን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ እና ኢትዮጵያ ያላትን ከፍታ ለማስቀጠልም  ”ኢትዮጵያ የራሷ ብራንድ ይገባታል” በሚል ዕሳቤ ትልቅ ራዕይ ይዞ በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በማስቀጠልም ግሩፑ ይዞት  የተነሳውን ተልዕኮ ለማሳካት ሰራተኛው  ጠንክሮ ሚናውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *