የጥራት ስራ አመራር ስልጠና ተሰጠ

የጥራት ስራ አመራር ስልጠና ተሰጠ። የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ በጋራ ያዘጋጁት ስልጠና ህዳር 13/2014 ዓ.ም ተሰጠ ::በጥራት ስራ አመራር ዙሪያ በተሰጠዉ በዚሁ ስልጠና የኢንዱስትሪ ሀላፊዎች፣ የመምሪያ ሀላፊዎችና ስታፊ ሀላፊዎች፣ በየደረጃዉ ያሉ የጥራት ስራ አመራር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል::የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ሀገራዊ የጥራት ስራ አመራር ስራን የሚደግፍፍ ተቋም እንደመሆኑ ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የደረጃዎች ተቋም የወሰደቻቸዉን ስታንዳርዶች የማሳወቅና ሰርተፋይድ የማድረግ ስራ ይሰራል:: ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ዋና መ/ቤቱን ጨምሮ በስታንዳርድና በጥራት መምራት የሚችል ለማድረግ በማለም የተሰጠ ስልጠና ነዉ:: የአምራች ተቋማትም ሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ህልዉና የሚረጋገጠዉ የሚገጥማቸዉን ተወዳዳሪነት በአሸናፊነት በመወጣት ላይ በመሆኑ ሲስተም ላይ የተመሰረተ እንዲሁም ሲስተሙ በጥራት የሚመራ ተቋም እንዲሆን እየተሰራ በመሆኑ የጥራት ስራ አመራር ወሳኙ ጉዳይ እንዲሆን ተገልጿል፡፡የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ቦንሳ ባይሳ ስልጠናዉን በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱን ሲስተም በማጠንከር ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር የምናደርገዉን ጥረት ማሳደግ ይኖርብናል ብለዋል፡፡የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋ/ ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸዉ ባስቀመጡት አቅጣጫ የከፍተኛ አመራሩ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የጥራት ስራ አመራርን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ከደረጃዎች ጋር እየተካሄደ ያለው ስራ የድርጊት መርሃ-ግብር ወጥቶለት እየተገመገመ በአጭር ጊዜ መሰራት ይኖርበታል ብለዋል።የደንበኞች እርካታ ለማረጋገጥ ብሎም በሀገር ዉስጥና በዉጭ ሀገር ተወዳዳሪ የሆነ ተቋም ለመፍጠር የጥራት ስራ አመራር መከተል ተገቢ መሆኑንም ኢንጂነር እንዳወቅ አብራርተዋል። የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመው በጋራ እየሰሩ ሲሆን አምስት ኢንዱስትሪዎች የISO ሰርተፍኬት እንዲያኙ እየተሰራ ይገኛል፡፡ስልጠናዉ ከመሰረታዊ የጥራት አመራር ዘዴ ፅንሰ ሀሳብ እስከ ስታንዳርድ ምንነት ያካተተ ሲሆን አስተባባሪዉ የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የጥራት ስራ አመራር አገልግሎት ነው::

https://www.facebook.com/eegroup/photos/pcb.1070849120395148/1070848847061842/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *